ችግሩን ለመፍታት ጥረት ላይ እየተደረገ ነዉ የሚለው የከተማው አስተዳደር በበኩሉ ” ሩጫ ላይ ነኝ ” ይላል።

የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች የውሀ ጀሪካኖች በጫኑ ባጃጆችና ጋሪዎች ተሞልተዉ ይታያሉ። ሆቴሎች የሻወር አገልግሎትን ከረሱ የቆዩ ይመስላሉ።

በአጠቃላይ ውሀ ቅንጦት መሆኑ ግለጽ ነዉ ይህን ጉዳይ ተመልክቶ የአካባቢዉን ማህበረሰብ ስለጉዳዩ የጠየቀዉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ሪፖርተር ችግሩ ለአመታት የቀጠለ መሆኑን ተረድቷል።

እንደነዋሪዎቹ ገለጻ የቧንቧ ውሀ በወር አንዴ በጣም ፈጠነ ሲባል በሁለት ሳምንት አንዴ ያውም ለሰአታት ብትመጣም አንዳንዴ የምትመጣዉ ሌሊት ሲሆን እንደምታመልጣቸዉ ይገልጻሉ።

ለሽንኩርትና ቲማቲም ከሚያወጡት እኩል ለውሀ ግዥ እንደሚያወጡ የሚገልጹት ነዋሪዎቹ መንግስት ችግራቸዉን ይቀርፍላቸዉ ዘንድ በምሬት ይጠይቃሉ።

በዚህ ጉዳይ ላይ ጠንካራ ጥያቄ ከሰሞኑ በነበረ የምክር ቤት ጉባኤ የቀረበለት የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በበኩሉ የውሀ ችግሮች ያለመፈታታቸዉ ምክኒያት በየዞንና ከተሞች የተጀመሩ የውሀ ጉድጓድ ፕሮጀክቶች እየተጀመሩ በመቆማቸዉ የተከሰተ መሆኑን ገልጾ የማህበረሰቡን ጥያቄ ለመመለስ በሙሉ ሀይሉ እንደሚሰራ ገልጾ ነበር።

ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ የህዝብ ጥያቄ  የቀረበላቸዉ የወልቂጤ ከተማ የውሀና ፍሳሽ አገልግሎት ቢሮ ሀላፊዉ  አቶ ዳዊት ሀይሌ በበኩላቸዉ ችግሩ መኖሩን በመግለጽ አሁን ላይ የቅሀ አጥረቱ ከተማዉን እየፈተነ መሆኑና ችግሩን ለመቅረፍ የተጀመሩ ስራዎች እንዳሉና ከሚጠበቁ መፍትሄዎች አንዱ የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ስራው ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ዳዊት አክለዉም ፤ በቅርቡ የጉራጌ ዞን የውሀና መአድን ቢሮ ጋር በመሆን ሁኔታዎች እንደሚገመገሙና ለህዝብ አስፈላጊዉ መረጃ እንደሚሰጥ በመግለጽ ሁኔታዉን ከከተማዉ ባለስልጣናት ባለፈ የዞኑም ሆነ የበላይ አካላት በትኩረት እየሰሩበት መሆኑን ጠቁመዋል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ፡-@tikvahethiopia

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *