21 ጥቅምት 2023

አትሌት ኬልቪን ኪፕተም ከአምስት ዓመታት በፊት በመጀመሪያው የአገር ውስጥ ይፋዊ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሆነው በውሰት ጫማ ነበር። እአአ 2018 ላይ የመሮጫ ጫማ የመግዛት አቅም ስላልነበረው በውሰጥ ጫማ የአትሌቲክስ ውድድርን የጀመረው አትሌት ዘንድሮ የማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት መሆን ችሏል። ኪፕተም በዘንድሮ የማራቶን ውድድር 2 ሰዓት 35 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት በመግባት የዓለም የማራቶን ክብረ ወንሰ ባለቤት መሆኑ ይታወሳል።በአትሌቲክስ ሕይወቴ ብዙ ውጣ ውረዶችን አሳልፊያለሁይላል የዓለም አትሌቲክስ የዓመቱ ምርጥ እጩ አትሌት ኬልቪን ኪፕተም ለቢቢሲ ሲናገር።የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት ለመሆን ያደረኩት ጥረት ቀላል አልነበረም። ሕልሜ እውን በመሆኑ በጣም ደስተኛ ነኝ። አሁን ሕይወቴ ተቀይሯል።ኪፕተም ከድሉ በኋላ ወደ አገሩ ሲመለስ ለሁለት ቀናት የዘለቀ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። ኪፕተም ወደ ቺካጎ ከማቅናቱ በፊት በሕመም እና በጉዳት ምክንያት በውድድሩ ላለመሳተፍ ከውሳኔ ለመድረስ ከጫፍ ደርሶ እንደነበረ ያስታውሳል።በዝግጅት ወቅት ሕመም አጋጥሞኝ ነበር። ጉዳት እንዲሁም የወባ በሽታ ይዞኝ ነበር። በውድድሩ መሳተፍ እንደማልችል ተስምቶኝ ነበር። ውድድሩ አንድ ሳምንት ብቻ ሲቀረው ከሕመሜ ማገገም ቻልኩ። ለአራት ወራት በዝግጅት በመቆየቴ በውድድሩ መሳተፍ እንደምችል ተሰማኝበማለት ያስረዳል።

የአትሌቱ አሰልጣኝ ጌርቫይስ ሃኪዚማና አትሌቱ በቺካጎ ማራቶን እንዲሳተፍ ሲወተውቱት ቆይተዋል። ሯዋንዳዊው የቀድሞ አትሌት፤ የአሁኑ አሰልጣኝ አትሌት ኪፕተምን ገና ልጅ እያለ እንደሚያውቁት ይናገራሉ።ገና ልጅ እያለ፤ በባዶ እግሩ ከብቶች ሲያግድ ነው የማውቀው። 2009 (እአአ) ላይ ከአባቱ እርሻ ጎን ልምምድ ሳደርግ አስታውሰዋለሁበማለት የትውውቃቸውን ጅማሬ ያስታውሳሉ። አትሌት ኪፕተም ከሕመሙ ካገገመ በኋላ በማራቶን ውድድሩ እንዲሳተፉ ማሳመን በመቻላቸው እና በዚሁ ውድድር ክብረ ወሰን በመስበሩ ትልቅ ደስታ እንደተሰማቸው አሰልጣኝ ሃኪዚማና ይናገራሉ። የሁለት ልጆች አባት የሆነው አትሌት ኪፕተም በኬንያ ብዙ ተስፋ ካላቸው እና በቅርቡ ብቅ ካሉ ባለ ብዙ ተስፋ የረዥም ርቀት ተወዳዳሪዎች መካከል አንዱ ነው።

ይህ አትሌት ከብዙዎች አትሌቶች የሚለየው አንድ እውነታ አለ። ብዙዎች ከመካከለኛ ርቀት የትራክ ውድድር በኋላ ፊታቸውን ወደ ማራቶን ውድድር ሲቀይሩ ይታያሉ። ኪፕተም ከአንድ ዓመት በፊት በጨራሽ በማራቶን ውድድር ተሳትፎ አያውቅም። ባለፉት ወራት ግን በሦስት የማራቶን ውድድሮች ተሳትፎ በሦስቱም ድል አድርጓል። ኪፕተም የማራቶን ውድድርን የመረጠው ወዶ ሳይሆን በገንዘብ እጦት ተገዶ መሆኑን ይገልጻል።በመሮጫ ትራኮች ላይ ለመለማመድ ገንዘብ የለኝም”“ልምምድ የማደርግበት ቦታ ከትራክ የራቀ ነው፤ በዚህም ምክንያት አስፓልት ላይ ከሌሎች ጋር መሮጥ ጀምሬ ወደ ማራቶን ገባሁይላል። አሰልጣኝ ሃኪዚማና አትሌት ኪፕተም መጀመሪያ ላይ በማራቶን ላይ የመሳተፍ ፍላጎቱ እምብዛም እንደነበረ ያስታውሳሉ። ኪፕተም ወደ አትሌቲክሱ የገባው የአጎቱን ልጅ ተከትሎ ነበር። ይህ የአጎቱ ልጅ ብዙውን ግዜ የአትሌት ኃይሌ /ስላሴ አሯሯጭ በመሆን ነበር የሚሮጠው። ኪፕተም ልቡ አትሌቲክስ ላይ ብትሆንም በተለይ ወላጅ አባቱ በትምህርቱ እንዲገፋ ነበር ፍላጎታቸው።አባቴ ኮሌጅ ገብቼ የኤሌክሪክ ባለሙያ ሆኜ እንድመረቅ ይፈልግ ነበር። እኔ ግን አትሌት የመሆን ጽኑ ፍላጎት ነበረኝበማለት ያስታውሳል። ግዜ ለእኔ በጣም ከባድ ግዜ ነበር። ምክንያቱም ለአራት ዓመታት ልምምድ ሳደርግ ብቆይም ምንም አይነት ስኬት አላስመዘገብኩም። እነርሱም (ወላጆቹ) በእኔ ተስፋ ቆርጠው ነበርይላል። ከኪፕተም የዓለም የማራቶን ክብረ ወሰን በኋላ ወላጅ አባት ልጃቸውንለዓላማው ጽኑ የሆነ ቆራጥ ልጅሲሉ ገልጸውታል።

ኪፕተም ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች መሮጥ ይችላል?

ኪፕተም በአትሌቲክሱ ብዙ እንዳይቆይ እንደ ስጋት የሚሆንበት ጉዳይ አለ። ይህም ፍጥነቱ ነው። በአንድ ወቅት አሰልጣኙ ኪፕተም በጉዳት በአጭር ግዜ ውስጥ ከአትሌቲክሱ ዓለም ሊርቅ እንደሚችል ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረው ነበር።በከፍተኛ ሁኔታ ልምምድ እያደረገ ነው። ፍጥነቱን እንዲቀንስ እነግረዋለሁ እርሱ ግን እንደዛ ማድረግ አይፈልግም። በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ በአምስት ዓመታት ውስጥ ሩጫ ሊያቆም እንደሚችል ነግሬዋለሁ። በአትሌቲክሱ ብዙ መቆየት ከፈለገ ፍጥነቱን መቀነስ አለበትብለዋል አሰልጣኝ ሃኪዚማና። ኪፕተም ግን ሃሳቡ ሌላ ነው። በቺካጎ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን መስበር መቻሉ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች መሮጥ የቻለ የመጀመሪያው ሰው መሆንን አስመኝቶታል። እአአ 2019 ላይ የምንግዜም ምርጡ የማራቶን ሯጭ ነው የሚባለው ኬንያዊው ኢሊዩድ ኪፕቾጌ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች መሮጥ ችሎ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ በውድድር የተደረገ ስላልሆነ ይፋዊ ሰዓት ተደርጎ አልተመዘገበለትም። ኪፕተም ሁልግዜም አርዓያ አድርጎ ከሚያየው ኪፕቾጌ ጋር የመሮጥ ፍላጎት እንዳለው ይገልጻል። ምናልባት ሁለቱ አትሌቶች በቀጣዩ የፓሪስ ኦሊምፒክ ላይ አብረው ሲሮጡ ልንመለከታቸው እንችላለን።አገሬን በኦሊምፒክ መድረክ የመወከል ዕድሉን ባገኝ የመጀመሪያዬ እንደመሆኑ ትልቅ ትርጉም ይኖረዋል። በኦሊምፒክ የሜዳሊያ ባለቤት የመሆን ሕልም ስላለኝ ትኩረቴ ሜዳሊያ ማግኘት ነውይላል።

ኢትዮ ካብ ስለሚሰጠው አገልግሎት ለማወቅ ድህረገጻችንን www.ethiocab.com ይጎብኙ

Driver application ለማውረድ http://driver.ethiocab.com  እንዲሁም Customer application ለማውረድ  http://user.ethiocab.com     

አብረን ሰርተን ትርፋችንን እንካፈል  !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *