![](https://ethiocab.com/wp-content/uploads/2023/09/7d94a770-55e5-11ee-ab8a-1dfa65e2455a.jpg)
መስከረም 6/2016 በአሜሪካዋ ኦሪገን፣ ዩጂን በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ የ5 ሺህ ሜትር ውድድር ጉዳፍ ጸጋዬ የዓለም ክብረ ወሰንን በማሻሻል አሸነፈች።
የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ10 ሺህ ሜትር አሸናፊዋ ጉዳፍ የትላንቱን ውድድር 14 ደቂቃ ከ00.21 በመጨረስ ነው ውድድሩን ያሸነፈችው።
ጉዳፍ በኬንያዊቷ ፌዝ ኪፕዬጎን ተይዞ የነበረውን የዓለም ሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ወድድር ክብረ ወሰን በ5 ሰከንዶች አሻሽላለች። ፌዝባለፈው ሰኔ ወር ላይ ነበር ፓሪስ ላይ በተደረገ ውድድር 14 ደቂቃ ከ05.20 ሰከንድ በመግባት ለ8 ዓመታት በገንዘቤ ዲባባ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን መስበር ችላ ነበር። ሆኖም ኬንያዊቷ ፌዝ ይዛው የነበረውን የርቀቱን ክብረ ወሰን ጉዳፍ ወደ 5 ሰከንድ ገደማ አሻሽላዋለች ፡፡ የውድድሩ የመጨረሻ ደውል ላይ በ12 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ ላይ የደረሰችው ጉደፍ የመጨረሻውን መስመር 14 ደቂቃ ከ00.21 ላይ አልፋዋለች። በዚህ ውድድር ኬንያዊቷ ቢትሪስ ቼቤት ጉዳፍን በመከተል በ14 ደቂቃ 05.92 ሰከንድ በመጨረስ የርቀቱን ሶስተኛ ፈጣን ሰዓት አስመዝግባለች። ኢትዮጵያዊቷ እጅጋየሁ ታዬ ደግሞ ውድድሩን በሶስተኝነት አጠናቃለች። በሌላ የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያዊ ዮሚፍ ቀጀልቻ በ3000 ሺህ ሜትር ውድድር በሁለተኝነት አጠናቋል። ይህንን ውድድር የ22 ዓመቱ ኖርዌያዊ ኢንግብሪትሰን በአንደኝነት አጠናቋል ። ኢትዮ ካብ ስለተመዘገበው ድል እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ ያለን ይላል ፡፡
ኢትዮ ካብ ስለሚሰጠው አገልግሎት ለማወቅ ድህረገጻችንን www.ethiocab.com ይጎብኙ
የ Driver application ለማውረድ http://driver.ethiocab.com እንዲሁም የ Customer application ለማውረድ http://user.ethiocab.com
ከኢትዮ ካብ ጋር መስራት ባለቤትነት ነው !!