![](https://ethiocab.com/wp-content/uploads/2023/10/d920a3c0-604c-11ee-a2cc-89c9f3fc75a6.jpg.webp)
1 ጥቅምት 2023
ኢትዮጵያዊቷ ድርቤ ወልተጂ በላቲቪያ መዲና ሪጋ ዛሬ መስከረም 20/ 2016 ዓ.ም በተካሄደው አንድ ማይል የዓለም የሴቶች የጎዳና ላይ ሩጫ ክብረ ወሰን ሰበረች። ድርቤ በ4፡21፡00 የዓለምን ሪከርድ በመስበር አንደኛ ስትወጣ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ፍሬወይኒ ኃይሉ ሁለተኛ በመውጣት ብር አግኝታለች። ፍሬወይኒ ኃይሉ 4፡23፡06 በመግባት የራሷን ምርጥ ሰዓት አስመዝግባለች። የአንድ ማይል ክብረ ወሰን ባለቤት የነበረችው እና ለአሸናፊነት ከፍተኛ ግምት የተሰጣት ኬንያዊቷ ፌይዝ ኪፕየጎን ደግሞ ውድድሩን በሦስተኛነት አጠናቃለች።
ባለፈው ዓመት መገባደጃ በቡዳፔስት በነበረው የዓለም ሻምፒዮና ውድድር ላይ በ1500 ሜትር የብር ሜዳሊያ ባለቤት የሆነችው የ21 ዓመቷ ድርቤ ይህንን ውድድር በድንቅ ብቃት እንዳጠናቀቀችም ተዘግቦላታል። ድርቤ ክብረ ወሰኑን ያሻሻለችው በቅርቡ በጀርመን በርሊን በተካሄደው 48ኛው የማራቶን ውድድር አትሌት ትዕግሥት አሠፋ የዓለም የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰንን ከሁለት ደቂቃ በላይ ማሻሿሏ ዓለምን እያነጋገረ ባለበት ወቅት ነው።
የ26 ዓመቷ አትሌት እንደ አውሮፓውያኑ 2019 በተካሄደው የችካጎ ማራቶን በኬንያዊቷ አትሌት ብሪጊድ ኮስጌ ተመዝግቦ የነበረውን 2:14.04 ከሁለት ደቂቃ በላይ አሻሽላለች። በዚህ የሪጋው ውድድር በአለም አቀፍ የሻምፒዮን ሺፕ ውድድሮች ላይ ብሮችን በማስመዝገብ የሚታወቀው ሐጎስ ገብረ ህይወት በ5 ኪሎሜትር በአንደኛነት ሥፍራ ውድድሩን አጠናቋል። ሐጎስ በዚህ ውድድር ላይ በ12፡59 ሰዓት አንደኛ የወጣ ሲሆን ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ዮሚፍ ቀጀልቻ በ2ኛነት ውድድሩን አጠናቋል። ዮሚፍ ውድድሩን ያጠናቀቀበት ሰዓት 13፡02 ሲሆን ሁለቱን ኢትዮጵያውያንንም ተከትሎ ኬንያዊው አትሌት ኒኮላስ ኪፕኮይር ሦስተኛ ሆኗል። አትሌቶቻችን እያስመዘገቡ ባሉት ድል የተሰማንን ውስጣዊ ደስታ እየገለፅን !
ኢትዮ ካብ አብረውን በመስራት የትርፍ ተጋሪ ይሁኑ ይላል !! አብረውን የትርፍ ተካፋይ ለመሆን ወይም ስለምንሰጠው አገልግሎት ለማወቅ ድህረገፃችንን www.ethiocab.com ይጎብኙ !!
የ Driver application ለማውረድ http://driver.ethiocab.com እንዲሁም የ Customer application ለማውረድ http://user.ethiocab.com
ከኢትዮ ካብ ጋር መስራት ባለቤትነት ነው!!