ኤልዶሬት በተባለችው የኬንያ ግዛት 15 የተቀቀለ እንቁላል የዋጠው የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊ መጨረሻ ሆስፒታል ሆኗል። ማንቸስተር ዩናይትድ ያሸንፋል ብሎ የአርሰናል ደጋፊ ከሆኑ ጓደኞቹ ጋር ውርርድ የገባው ቶማስ ኪፑታኒ ኬምቦይ ዩናይትድ ከተሸነፈ 30 የተቀቀለ እንቁላል ለመብላት መወራረዱን የኬንያ መገናኛ ብዙኃን ፅፈዋል። ባለፈው እሑድ አርሰናል በኤሜሬትስ ስታድየም ማንቸስተር ዩናይትድ ሲያስተናግድ ነው ይህ የሆነው።

ዩናይትድ በጨዋታው 3-1 መረታቱን ተከትሎ አንድ ሙሉ ትሪ እንቁላል ለመዋጥ ቃል የገባው ኬምቦይ ከጨዋታው በኋላ ቃሉን መፈፀም ይጀምራል። ማሕበራዊ ሚድያ ላይ የተሰራጩ ምስሎች ግለሰቡ ጓደኞቹ እያበረታቱት በየመሐሉ ውሃ እየጠጣ የተቀቀለ እንቁላል ሲውጥ ያሳያሉ።  ሲቲዝን የተሰኘው ሚድያ እንደዘገበው ኬምቦይ 15ኛው እንቁላል ላይ ሲደርስ ራሱን ስቶ ሲወድቅ ጓደኞቹ እየቀለደ መስሏቸው ሲሳሳቁ ነበር። ግለሰቡ ራሱን ስቶ መውደቁን የተረዱት ጓደኞቹ ከወደቀበት አፋፍሰው ወደ ሆስፒታል ይዘውት ይሄዳሉ። የሲቲዝን ዘገባ እንደሚያሳየው ካፕኬኖ በተሰኘ ቅፅል ስሙ የሚታወቀው የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊ ሆስፒታል ከገባ በኋላ ተመርምሮ የሆድ ድርቀት እንዳለበት ታውቋል።  ከሕመሙ እስኪያገግም ድረስ ሆስፒታል ቆይቶ ጤናው መለስ ሲል እንደወጣ የኬንያ መገናኛ ብዙኃን አስነብበዋል።  “መጀመሪያ በጣም ደስ ብሎኝ እንቁላሉን ስበላ ትዝ ይለኛል። ከዚያ ስነቃ ሆስፒታል ውስጥ ራሴን አገኘሁት። አሁን ጤናዬ ስለተመለሰ ደስተኛ ነኝ” ሲል ካፕኬንኮ ስታንዳርድ ለተሰኘው ጋዜጣ ተናግሯል። ሁሌም ቢሆን ስሜታዊ ሆነን የምንወስናቸው ውሳኔዎች መዘዛቸው በጣም የከፋ ሊሆን ይችላል ስለዚህ ሁል ጊዜ የምናደርጋቸው ነገሮችን በማስተዋል እናድርግ ይለናል ኢትዮ ካብ !! ኢትዮ ካብ ስለሚሰጠው አገልግሎት ለማወቅ ድህረገጻችንን  www.ethiocab.com ይጎብኙ

የ Customer application ለማውረድ  http://user.ethiocab.com እንዲሁም

የ Driver application ለማውረድ http://driver.ethiocab.com ያገኙናል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *