የኢትዮጵያ ሴቶች ማኀበር ሴቶች ላይ እየደረሱ ናቸው የተባሉ ፈርጀ ብዙ ችግሮችን በተመለከተ በየክልሉ በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማትን በመጋበዝ ትላንት ረቡዕ በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር።
በዚህም ላይ ከተገኙት ባለድርሻ አካላት መካከል የአማራ ክልል ሴቶች ማኀበር አንዱ ነው።
በአማራ ክልል በ “ፋኖ” ታጣቂዎችና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በየወቅቱ እያገረሸ የሚስተዋለውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚስተዋለው ሞት እየጨመረ መሆኑን፣ ሴቶችም ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች እየተበራከቱ መሆኑን የክልሉ ሴቶች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የክልሉን ሴቶች ማኀበር ወክለው የመጡ ወ/ሮ በላይነሽ ሽባባው ምን አሉ ?
➡ ከጤና ጋር ተያይዞ የእናቶች ሞት፣ የሕጻናት ሞት ከበፊቱ በጣም እየጨመረ መጥቷል።
➡ በጣም በርካታ ሴቶች ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ ጥቃት እየደረሰባቸው ነው። አንደኛ ፍትህ የሚያገኙበት አጋጣሚም የለም። ሁለተኛ ደግሞ ከጦርነቱ ዘለው ወደ IDP center እንኳን ሲገቡ እዚያው ውስጥም መልሶ ጥቃት የሚያጋጥምበት ሁኔታ አለ።
➡ ሰላም አስካልተጠበቀ ድረስ ሴቶች ነገም፣ ከነገ በኋላም የጥቃቱ ሰለባ ናቸው። በአጠቃላይ እንደ አገራችን፣ እንደ አማራ ክልልም ሴቶች ጥቃት እየደረሰባቸው ያለው ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ነውና የሴቶች አደረጃጀቶች ሰላምን ከማስጠበቅ አንጻር ጎልተው መውጣት አለባቸው።
➡ አማራ ክልል ራሱ የበፊቱን እንኳን ትተነው አሁን በሚስተዋለው ግጭት ብቻ ከ4,000 በላይ ሴቶች ተደፍረዋል። ስለዚህ በዋናነት ይህን ጥቃት ለማስቆም መስራት ያለብን ሰላሙ ላይ ነውና በተለይ የሴቶች አደረጃጀት ደግሞ በጋራ ሆነው መንግሥትን፣ ሌላውንም አካል በማወያየት ሰላሙ ላይ ብንሰራ የሴቶችን ጥቃት መቀነስ ይቻላል.
በትላንቱ መርሀ ግብር የተለያዩ ተቋማትን ወክለው የተገኙ ኃላፊዎች በበኩላቸው ማኀበራቱ ሁሉ በጸጥታ ወቅት የሚፈጸሙ ፆታዊ ጥቃቶችን በተመለከተ ቅንጅት በሠፍጠር ልዩ ትኩረት እንዲሰጥበት በውይይታቸው አንስተዋል።
በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon
ምንጭ ፡-@tikvahethiopia