6 ህዳር 2023

ኮሎምቢያዊው የሊቨርፑል ተጫዋች ሉዊስ ዲያዝ አጋቾች አባቱን እንዲለቀቱናከስቃይ እንዲገላግሉትተማፅኗል። ግራ ዘመሙ ሽምቅ ተዋጊ ብሔራዊ ነፃነት ግንባር [ኢኤልኤን] ከቀናት በፊት የሉዊስን እናትና አባት ባራንካስ በተባለ ሥፍራ አፍነው መውሰዳቸው ይታወሳል። ነገር ግን እናቱ ቢገኙም አባቱ አሁንም አድራሻቸው አይታወቅም። እሑድ ከሉተን ሊቨርፑል ከሉተን ታውን በነበረው ጨዋታ ጎል ያስቆጠረው ሉዊስ ዲያዝነፃነት ለአባቴየሚል በስፔንኛ የተፃፈ መልዕክት ካናቴራው ላይ አስነብቧል።በእያንዳንዷ ሰከንድና ደቂቃ ጭንቀታችን እየጨመረ ነውሲል 26 ዓመቱ የክንፍ መስመር ተጫዋች ከጨዋታው በኋላ በለቀቀው መግለጫ ገልጧል።እናቴ፣ ወንድሞቼና እና እኔ በጣም ጨንቆናል፣ ጠቦናል። የሚሰማንን ለመግለጥ ቃላት ያጥረናል። ይህ ስቃያችን የሚያበቃው አባታችን ቤት ገብቶ ስናየው ነው።ፅናቱን አክብረው አባቴን እንዲለቁትና ከስቃይ እንዲገላግሉን እማፀናቸዋለሁ። በፍቅርና መተሳሰብ ስም ድርጊታቸውን አጢነው አባታችንን እንዲመልሱልን እንጠይቃለን።ዲያዝ አክሎበዚህ አስጨናቂ ጊዜ ኮሎምቢያዊያንና ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ላደረጉልኝ ድጋፍና ትብብር አሰመግናለሁብሏል። የኮሎምቢያ መንግሥት የተጫዋቹ አባት ሉዊስ ማኑዌል ዲያዝን ለማስለቀቅ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶችና ወታደሮች አሰማርቷል። የዲያዝ ቤተሰቦች በታፈኑ ወቅት አንድ የደኅንነት ካሜራ ሞተር ብስክሌት የሚነዱ ሰዎች የተጫዋቹን ቤተሰቦች መኪና ሲከታተሉ አሳይቷል። በላ ጉዋሂራ አውራጃ ባራንካስ በተባለ ሥፍራ መኪናቸውን አቁመው ነዳጅ ሲቀዱ ነው የታፈኑት። አፋኞቹ ፖሊስ ያሉበትን አፈላልጎ ሲደርስባቸው የዲያዝና እናት መኪና ውስጥ ጥለው አባቱን ይዘው አምልጠዋል።

የሃገሪቱ ፖሊስ መጀመሪያ የወንጀሎች ስብስብ ለድርጊቱ ተጠያቂ ነው ብሎ ነበር። በኋላ ግን ከአማፂው ቡድን ጋር ድርድር ላይ ያለው የመንግሥት ተወካይ የተጫዋቹን ወላጆች ያፈኑትየኢኤልኤን አባላት እንደሆኑ ኦፊሴላዊ መረጃ አለንብሏል።  የአማፂው ቡድን ተወካይ በጥቂት ቀናት የዲያዝ አባት እንደሚለቀቁ መናገራቸው ተዘግቦ ነበር። ኢኤልኤን ኮለምቢያ ውስጥ ካሉ ሽምቅ ተዋጊ ቡድኖች ከቀደምቱ አንዱ ነው። ከአውሮፓውያኑ 1964 ጀምሮ መንግሥትን ሲዋጋ የቆየው ይህ ቡድን 2500 አባላት አሉት። ቡድኑ የዲያዝ ወላጆች በሚኖሩበትና ኮሎምቢያ ከቬንዝዌላ ጋር በምትዋሰንበት አካባቢ ይንቀሳቀሳል።

ኢትዮ ካብ ስለሚሰጠው አገልግሎት ለማወቅ ድህረገጻችንን www.ethiocab.com  ይጎብኙ

Driver application ለማውረድ http://driver.ethiocab.com  እንዲሁም Customer application ለማውረድ  http://user.ethiocab.com   

አብረን ሰርተን ትርፋችንን እንካፈል  !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *