ከአመታት በፊት ጠቅላላ ሃኪም እያለው የገጠማኝን ላካፍላችሁ

 ትንሽ ቆየት ብሏል አንድ ታዋቂ ሁላችንም የምንወደው አርቲስት ያርፋል። በሰዓቱም ብዙ ሚዲያ የስፖርት ጋዜጠኞች ሳይቀሩ አርቲስቱቶንሲል ታሞ ሂዶ በህክምና ስህተት አረፈ!” ብለው ዘገቡትማንሳት የፈለኩት እሱን አይደለም። ማንሳት የፈለኩት ይህ በሆነ 3 ቀኑ ወደምሰራበት ሆስፒታል 7 አመት ልጇን ይዛ ስለመጣች እናት ነው። ይህች እናት ልጇ ከፍተኛ ትኩሳት እንዳለውና እና ምግብ መዋጥ እንዳቃተው ታስረዳናለች ቶንሲሉም አብጦ መግል ሚመስሉ ጠብታዎች ይታዩበት ነበር።  የላብራቶሪ ውጤቱ ሁሉም “Acute Tonsilopharyngitis” በተለምዶቶንሲልሚባለው ህመምን ያመላክተናል። ይህ በሽታ ደሞ በመድሃኒት እንደሚድን በጊዜ ካላሳከመችው ሊከሰት ሚችሉ ጉዳቶችን በልመና መልክ ደጋግመን ስንነግራት ድንገት ቱግ አለች

ልጄን ልትገሉብኝ!” ብላ በእናትነት ልብ ለልጇ ሳሳችይዛው ቤት ሄደች።  ከዚያ በኋላ ልጁ ህክምናውን እንዳልወሰደ እንጂ ቤት ውስጥ ምን እንደተፈጠረ አላውቅም። ሁኔታው ግን በጣም ያስገረመኝ 2 ወራት ገደማ በኋላ ነበር። ድንገት የህፃናት ተኝቶ መታከሚያ ውስጥ ስገባ ይህ ህፃን አልጋ ይዞ ሲታከም አየሁት።

ይህን ልጅ አውቀዋለው‘! ብዬ ተጠጋሁ።  እናትየው ተሰብራ ጭምት ብላ ከጎኑ አገኘዋት።

የልብ ህመም ነው ብለውኝ ተኝቶ እየታከመ ነው። ምንም ለውጥ የለውም አለቺኝ አዝኜ ሄድኩ

ይህ ቶንሲል ሚያመጡ group A Streptococcus ሚባሉ ባክቴሪያዎች በጊዜ ካልታከሙ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ autoimmune በሚባል ሂደት Rheumatic Fever የሚባል የልብ በሽታን የማምጣት አቅም አላቸው። የልጁም ህመም ይህ ነበር። አሁንም ይህ የልብ ህመም በበቂ ካልታከመ ወይንም ከመታከሙ በፊት ሰፊ ጉዳት ካደረሰ የማይድን የልብ ህመም / Heart failure ውስጥ ይከታል ባስ ካለም ይገላል።  ሁሌም በሚዲያ፣ በአሉባልታ፣ በመሰለኝ እና በይሆናል የምንወስናቸው የጤና ውሳኔዎች ከጊዜ በኋላ የሚያመጡብን መዘዝ አይታወቅምና። መረጃዎችን እንመርምር! አንድ ሀኪም የገጠመውን ሲናገር ነበር እንዲህ ያለው ይሄን በተደጋጋሚ በሀገራችን እየሰማነው እና እየተከሰተ ያለ ሁኔታ ነበር ፡፡ ኢትዮ ካብ ሁሌም ሳንዘናግ በተለይ ጤናችንን በተመለከተ ሁሌም ሀላፊነት እንውሰድ እንዲሁም አንዘናጋ ይለናል !! የኢትዮ ካብ የትርፍ ተካፋይ ለመሆን እንዲሁም ስለሚሰጠው አገልግሎት ለማወቅ ድህረገፃችንን www.ethiocab.com ይጎብኙ !!

የ Driver application ለማውረድ http://driver.ethiocab.com  እንዲሁም የ Customer application ለማውረድ  http://user.ethiocab.com   

ኑ አብረን የሰራነውን አብረን እንካፈል የሚለን ኢትዮ ካብ ነው !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *