![](https://ethiocab.com/wp-content/uploads/2023/09/99e3d720-5ec8-11ee-93e8-5d16174eb488.jpg.webp)
29 መስከረም 2023
ከሳር ተሰርቶ ስድስት ሺህ ዓመታት ገደማ ዕድሜ አለው ተብሎ የተገመተ ጥንታዊ ጫማን በስፔን በአንድ ዋሻ ውስጥ ማግኘቱን ተመራማሪዎች አስታወቁ። በአውሮፓ ውስጥ ከተገኙ ቀደምት ጫማዎች መካከል በእድሜ ቀዳሚ ነው የተባለው ይህ ጫማ ስፔን ውስጥ በሚገኝ የሌሊት ወፎች ዋሻ ውስጥ ነው የተገኘው። በ19ኛው ክፍለ ዘመን በማዕድን አውጪዎች ተዘርፏ ከተባለው ዋሻ ውስጥ በርካታ የተለያዩ አይነት ጥንታዊ ቁሶች ከጫማው በተጨማሪ በተመራማሪዎቹ ተገኝተዋል። በዋሻው ውስጥ ያለው ዝቅተኛ እርጥበት እና ነፋስ ባልተለመደ ሁኔታ ጥንታዊ ቁሶቹን ሳይበለሳሹ እንዲቆዩ እንዳደረጋቸው ባለሙያዎቹ ገልጸዋል። ተመራማሪዎቹ የተለያዩ አይነት ጥንታዊ ቁሳቁሶችን እና ቅርጫቶችን መርምረዋል። በምርምሩ ተሳታፊ የሆኑት ማሪያ ኦታል የተገኙት ቁሶች “እስካሁን በደቡባዊ አውሮፓ ባሉበት ሁኔታ መገኘታቸው ከታወቁ የዕፀዋት ውጤቶች መካከል በዕድሜ ቀዳሚዎቹ ናቸው” ብለዋል። ጨምረውም እነዚህ ግኝቶች ላይ “ጥቅም ላይ የዋሉት የተለያዩ አይነት ዘዴዎች እና የጥሬ ዕቃዎች አዘገጃጀት ረገድ ቅድመ ታሪክ ማኅበረሰቦች ያላቸውን ክህሎት ለማየት ይቻላል” ሲሉ ተናግረዋል። በዋሻው ውስጥ የተገኙትን 76 ቁሶች ዕድሜ ለማወቅ ጥቅም ላይ የዋለው አዲስ ቴክኖሎጂ እንዳረጋገጠው፣ ቀደም ሲል ከተገመተው በላይ የ2,000 ዓመት ዕድሜ እንዳላቸው ተገልጿል። አንዳንዶቹ ቁሶችም 9,000 ዓመት ያህል እድሜ እንዳላቸው ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል። በተገኘው ነጠላ ጫማ ላይ በተደረገው ምርምር ጫማውን ለመሥራት የተለያዩ የሳር አይነቶች ጥቅም ላይ ከመዋላቸው በተጨማሪ ቆዳ እና ኖራ ተገኝቶበታል ተብሏል። ይህ ግኝትም በአውሮፓውያኑ 2008 አርሜኒያ ውስጥ ከተገኘው እና 5,500 ዓመታትን ካስቆጠረው ጫማ በላይ ዕድሜ ያለው መሆኑ ተገልጿል። ስድስት ሺህ ዓመት ዕድሜ አለው የተባለው ጫማ የተገኘበት ዋሻ በደቡባዊ ምዕራብ ስፔን አንዳሉሺያ ግዛት ውስጥ “የሌሊት ወፎች ዋሻ” በመባል በሚታወቀው ስፍራ ነው። በተመራማሪዎቹ ጥናት መሠረት ሰው መጀመሪያ ላይ ወደ ዋሻው የገባው በ1831 የአፈር ማዳበሪያ ለማዘጋጀት የሌሊት ወፎችን ዐይነ ምድር ለመሰብሰብ ነበር። ከዚያም በኋላ ማዕድን አውጪዎች ወደ ዋሻው በመግባት የተለያዩ ጥንታዊ ቅርሶችን ለማግኘት መቻላቸው ይነገራል። ብለዋል።ገልጿል። የሚወጡ አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት ድህረገፃችንን ይጎብኙ እንዲሁም ኢትዮ ካብ ስለሚሰጠው አገልግሎት ለማወቅ ድህረገፃችንን www.ethiocab.com ይጎብኙ !!
የ Driver application ለማውረድ http://driver.ethiocab.com እንዲሁም የ Customer application ለማውረድ http://user.ethiocab.com
ኑ አብረን የሰራነውን አብረን እንካፈል የሚለን ኢትዮ ካብ ነው !!