15 ህዳር 2023

ኢትዮጵያ 2026 የአሜሪካ የዓለም ዋንጫ እንድታልፍ እፈልጋለሁ። የማይሳካ ቢመስልም ዕድል አለን።ዮሐንስ ዘውዴ ከኮከብ ተጫዋቾች ጋር መቀራረብ ያለውን ጥቅም ከብዙዎች በላይ ያውቃል። 1980ዎቹ አዲስ አበባ ተወልዶ ያደገው ዮሐንስ አስገራሚ ታሪክ አለው። 10 ዓመቱ ከእናቱ ጋር ወደ ላስ ቬጋስ አቀና። ከዝቅተኛው የቬጋስ እርከን ላይ በመነሳት ለታዋቂ ስፖርተኞች የእረፍት ጊዜ አሳማሪ ለመሆን በቅቷል። በማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ ጭምር ነው። አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ስትራቴጂክ አማካሪ በመሆን ይሠራል።በዚህ ሚና ላይ አሁን አራት ወር ሆኖኛል። ሥራዬ በፌደሬሽኑ እና በሌሎች ሊጎች፣ በፌዴሬሽኖች እና በብራንዶች መካከል መቀራረብን በመፍጠር ድልድይ መሆን ነውሲልጆኒ ቬጋስበመባል የሚታወቀው ዮሐንስ ለቢቢሲ ስፖርት ተናግሯል።በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ብርሃን ለመፈንጠቅ፣ በአገራችን ያለውን እምቅ አቅምና ያለንን ሐብት እና ገጽታ ለለዓለም በማሳየትመጥታችሁ ኢንቨስት ብታደርጉ አስደናቂ ነገር ታገኛላችሁማለት ነውሲል ስለ ኃላፊነቱ ገልጿል።ይህን ስፖርት የሚወዱ ብዙ ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶች አሉን። ትንሽ ማበርታት እና ትንሽ ዕድል ብቻ የሚፈልጉ ናቸው።ከፓርኪንግ ሠራተኛነት እስከ እግር ኳስ ተጫዋች የእረፍት ፕሮግራም አቃጅነት ዮሐንስ አዲሱ ሙያው የተገናኙት ብዙዎች በማይገምቱት ምመልኩ ነው። በታዋቂው ቤላጂዮ ሆቴል እና ካሲኖ ውስጥ የመኪና ፓርኪንግ ሠራተኛ ይሠራ ነበር።ምርጥ ጊዜ ነበር። እንደ ሊዮናርዶ ካፕሪዮ፣ ፍሎይድ ሜይዌዘር እና ማይክል ጆርዳን ያሉ ሰዎችን አይቻለሁይላል 36 ዓመቱ ዮሐንስ።

በአንድ ወቅት አንድ ፈረንሳዊ የፊልም ተዋናይ መኪናውን አስነስቶ ሊወታ ሲል አገኘሁት። በጣም የምወደው ተጫዋች ፍራንክ ሪበሪ እንደሆነ ነገርኩት። እሱም ሪቤሪ ወንድሜ እንደማለት ነው አለኝ።በሚቀጥለው ዓመት ስንገናኝ ግለሰቡ ሪቤሪ የፈረመበትን ማልያ እና ቁምጣ አመጣልኝ። ከዚያ በኋላ አንድ እኔ [የምንከባከበው] ሰው እንዳለ ነገረኝ። ጓደኛው በሆቴሉ ሲቀመጥ በምስጋና መልክ ክፍያውን ፈጸምኩኝ።የነበረውን ነገር ጓደኛው ለተዋናዩ ነገረው። ተዋናዩሁለት ወር ስጠኝ ላንተ ድንቅ ነገር አግኝቻለሁአለኝይላል።

ከሁለት ወር በኋላ እቤት ከእናቴ ጋር ኦፕራን ስንመለከት ስልክ ተደወለልኝ።ሃይ፣ ናስሪ ነኝ፣ ስለተዋወቅን ደስ ብሎኛልአለኝ። እሱና እና ጓደኞቹ ወደ ቩጋስ እንደሚመቱ ነግሮ አንዳንድ ነገሮችን አመቻችቼ እጠብቀው እንደሆነ ጠየቀኝ።””ሳሚር ናስሪ አውቀው እንደሆነ እስከሚጠይቀኝ ድረስ አላወቅኩትም ነበር። ገረጣሁ፣ ተንቀጠቀጥኩ፣ አላበኝሲል አጋጣሚውን ያስታውሳል።ከዚያ በኋላ አንዱ ሌላውን መሳብ ጀመረ። ቲዎ ዋልኮት፣ ባካሪ ሳኛ፣ ኬራን ጊብስ እና መላው የአርሰናል ቡድን መጣ። የዮሐንስ ከበርካታ ስመ ጥር ሰዎች ጋር ሰፊ ትስስር ፈጥሯል። የኩባንያው የክሎውዳውት ስኬት እና በማህበራዊ ሚዲያዎች ያሉት ተጽእኖ በርካታ ዕድሎችን ፈጥሮለታል። በሰይፉ ፋንታሁን ሾው ላይ ለመታየትም በቅቷል።  መሠረቱን ግን አልረሳም። ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ፤ ሲሄድ ጀምሮ ነበሩ ችግሮች አሁንም ባሉበት መኖራቸውን ተመለከተ። ያወጣው ዕቅድም ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ደጃፍ የሚያደርሰው ነበር።እነዚህን አርአያ እና ለብዙ ኢትዮጵያዊን ህጻናት ኮከብ ከሆኑ ስፖርተኞች ጋር በመሥራት ስኬታማ ሆኛለሁሲል ያስረዳል።ልጅ እያለሁ በእነሱ ደረጃ ለመሆን እፈልግ እንደነበር አስታውሳለሁ። እኔ እዚያ ደረጃ ብደርስም ወደ ሀገሬ ስመለስ አሁንም ተመሳሳይ ችግሮች እንዳሉ አይቻለሁ።

በእግር ኳስ በኩል ለሰዎች ዕድሎችን ማምጣት ፈልጌ ነበር። ስለዚህ ግንኙነቴን በመጠቀም ሁሉም ሰው የማደግ ዕድል እንዲያገኝ ለመሥራት ከፌዴሬሽኑ ጋር ተነጋገርኩኝ። በእኔ ሃሳብ ተስማምተው የዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራን ሰጡኝ። የኢትዮጵያን እምቅ ሃብት መጠቀም በውጤት ረገድ የኢትዮጵያ የወንዶች ብሔራዊ ቡድን የተለያየ መልክ አለው።  ዋሊያዎቹ በፊፋ የዓም ዋንጫ ተሳትፈው አያውቁም። በአፍሪካ ዋንጫ ለመጨረሻ ጊዜ ከምድብ ድልድል ያለፉት ኢትዮጵያ ባዘጋጀችው 1968 የአፍሪካ ዋንጫ ነው። በውድድሩ አራተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።  አሁን ያለው ቡድን በሜዳው ከተጫወተ ከሁለት ዓመት በላይ ሆኖታል። ይህ የሆነው ባህር ዳር ስታደየምን ጨምሮ በአገሪቱ ያሉ 21 ስታዲሞች በቂ መሠረተ ልማቶች አላሟሉም በሚል በመታገዳቸው ነው።  ቡድኑ በሜዳው ሊያደርግ የሚገባቸውን የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪኣ ጨዋታዎች በማላዊ፣ ሞዛምቢክ እና ሞሮኮ አከናውኗል። ዛሬ 2026 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከሴራሊዮን ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ በሞሮኮ ያከናውናል። እዚህ ጋር ነው ዮሐንስ ትልቅ ተጽዕኖ መፍጠር እንደሚችል የሚያምንበት ቦታ ነው።በእርግጥ እኔ አሰልጣኝም፣ ቴክኒካል ዳይሬክተርም አይደለሁምይላል።ኃላፊነቴ አገሮችን፣ ሊጎችን እና ብራንዶችን ከፌዴሬሽኑ ጋር ግንኙነት እንዲፈጥሩ ማድረግ ነው። በአሁኑ ወቅት በደጋፊዎቻችን ፊት አለመጫወታችን ይጎዳናል። ስለዚህ አሁን ብሔራዊ ቡድኑን መደገፍ ትልቅ ነገር ነው።“”ለተጫዋቾችም ተጨማሪ ሃብቶችን ያመጣልለ። የሚያሠለጥኑበትን ቦታ እንዲያገኙ በሮች ይከፈታል። ዝግጅታቸውን ያሻሽላል። የእኔ መኖር ያንን የስነ ልቦና ድጋፍ ለመስጠት ነውየዮሐንስ ድጋፍ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ያደርጋታል ወይ የሚለው ወደፊት የሚታይ ቢሆንም የሚለፋው ግን ሞከረ ለመባል ብቻ አይደለም። እናምጆኒ ቬጋስዕድሎቹን በሞከረ ቁጥር ሁሉም ነገር ይቻላል።

ኢትዮ ካብ ስለሚሰጠው አገልግሎት ለማወቅ ድህረገጻችንን www.ethiocab.com ይጎብኙ

Driver application ለማውረድ  http://driver.ethiocab.com  እንዲሁም Customer application ለማውረድ  http://user.ethiocab.com    

አብረን ሰርተን ትርፋችንን እንካፈል  !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *