መስከረም 6/2016 በአሜሪካዋ ኦሪገን፣ ዩጂን በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ 5 ሺህ ሜትር ውድድር ጉዳፍ ጸጋዬ የዓለም ክብረ ወሰንን በማሻሻል አሸነፈች።

የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና 10 ሺህ ሜትር አሸናፊዋ ጉዳፍ የትላንቱን ውድድር 14 ደቂቃ 00.21 በመጨረስ ነው ውድድሩን ያሸነፈችው።

ጉዳፍ በኬንያዊቷ ፌዝ ኪፕዬጎን ተይዞ የነበረውን የዓለም ሴቶች 5 ሺህ ሜትር ወድድር ክብረ ወሰን 5 ሰከንዶች አሻሽላለች። ፌዝባለፈው ሰኔ ወር ላይ ነበር ፓሪስ ላይ በተደረገ ውድድር 14 ደቂቃ 05.20 ሰከንድ በመግባት 8 ዓመታት በገንዘቤ ዲባባ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን መስበር ችላ ነበር። ሆኖም ኬንያዊቷ ፌዝ ይዛው የነበረውን የርቀቱን ክብረ ወሰን ጉዳፍ ወደ 5 ሰከንድ ገደማ አሻሽላዋለች ፡፡ የውድድሩ የመጨረሻ ደውል ላይ 12 ደቂቃ 55 ሰከንድ ላይ የደረሰችው ጉደፍ የመጨረሻውን መስመር 14 ደቂቃ 00.21 ላይ አልፋዋለች። በዚህ ውድድር ኬንያዊቷ ቢትሪስ ቼቤት ጉዳፍን በመከተል 14 ደቂቃ 05.92 ሰከንድ በመጨረስ የርቀቱን ሶስተኛ ፈጣን ሰዓት አስመዝግባለች። ኢትዮጵያዊቷ እጅጋየሁ ታዬ ደግሞ ውድድሩን በሶስተኝነት አጠናቃለች። በሌላ የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያዊ ዮሚፍ ቀጀልቻ 3000 ሺህ ሜትር ውድድር በሁለተኝነት አጠናቋል። ይህንን ውድድር 22 ዓመቱ ኖርዌያዊ ኢንግብሪትሰን በአንደኝነት አጠናቋል ።        ኢትዮ ካብ ስለተመዘገበው ድል እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ ያለን ይላል ፡፡

ኢትዮ ካብ ስለሚሰጠው አገልግሎት ለማወቅ ድህረገጻችንን www.ethiocab.com ይጎብኙ

የ Driver application ለማውረድ http://driver.ethiocab.com እንዲሁም የ Customer application ለማውረድ  http://user.ethiocab.com

ከኢትዮ ካብ ጋር መስራት ባለቤትነት ነው !! 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *