እንግሊዛዊው ማይክል ካሮል ህይወትን ለማሸነፍ ፡ የሚረዳውን ስራ ሲፈልግ ፡ሲወጣ፡ሲወርድ ቆየ ።ግን ለሱ የሚሆን ስራ የለም ።ለሱ የሚሆን ስራ ያለው አንድ ቦታ ብቻ ነው ። የእንግሊዝ መዘጋጃ ቤት እና የሎንዶን ከተማ ፡ መዘጋጃ ቤት የፅዳት ሰራተኞችእንደሚፈልግ ያወጣውን ክፍት የስራ ቦታ አይቶ ሄዶ ተመዘገበ ። ከቀናት በኋላም ተቀጠረ ። ማይክል ይህንን ስራ በመስራት ላይ እያለ ፡ አንድ ቀን ካገኛት ገንዘብ ላይ ቆጥቦ ሎተሪ ቆረጠ ።

ፈጣሪ በ19 አመትህ የለንደን ከተማ ፅዳት ሰራተኛ ሆነህ አትቅር ሲለው ፡ የቆረጠው ሎተሪ ደርሶት. .. የ18 ሚሊዮን ዶላር አሸናፊ ሆነ ። ማይክል ካሮል ፡ ከፅዳት ሰራተኝነት ፡ በአንድ ጊዜ ሚሊየነር ሆነ ። ህይወት ሳቀችለት ።  ቤት ገዛ ፡ መኪኖች ኖሩት ።  ስራ የሚባል ነገር አለርጂኩ ሆነ ። ጠዋት ይነሳል ፡ ሲጠጣ ይውላል ፡ ከብዙ ሴቶች ጋር መዋል ፡ ድራግ መጠቀም ጀመረ ።አኗኗሩ ቅጥ አጣ ። በተለያዩ ወንጀሎች እየተከሰሰ ፡ ፍርድ ቤት መቅረብ ስራው ሆነ ። በዚህም ከሰላሳ ያላነሱ ጊዜያት በተለያዩ ትናንሽ ወንጀሎች ተከሶ ፍርድ ቤት ቀርቦ ፡ በገንዘብ እና በቀላል እስር ይቀጣ ነበር ። ማይክል የአልኮል ሱሰኝነቱ ከመብዛቱ የተነሳ በቀን ፡ ሁለት ጠርሙስ ቮድካ ይጠጣ ነበር ። በአንድ ወቅት የለንደን ከተማ ፅዳት ሰራተኛ ሆኖ  ድህነትን እንዳላጣጣማት ያሳለፈውን መጥፎ ጊዜ ረስቶ ፡ 24/7 ገንዘቡን መርጨት ጀመረ ። በዚህ ሁኔታ ጥቂት አመታት ካለፉና ፡ በእጁ የነበረው ገንዘብ እንዳልነበር ከሆነ  በኋላ ማይክል ስራ መስራት እንዳለበት አሰበ ። ለአመታት ስራ የሚባል ነገር ትቶ መኖሩ ቆጨው ። እና አንድ ቀን ጠዋት ተነስቶ ወደ አንድ ቢሮ ሄዶ አንኳኳ ሃላፊው እንዲገባ ፈቀዱለት  እንዴት ኖት አላቸው ። ሰውየው ምቾት የለወጠውን ማይክልን በቶሎ ማስታወስ አልቻሉም ።

እርግጥ ነው ጊዜው ስለቆየ ረስተውኝ ይሆናል ። እኔ ማይክል ካሮል እባላለሁ ። ከአመታት በፊት እናንተ ጋር እሰራ ነበር ። እና አሁን የመጣሁት ክፍት ቦታ ካለ ለመቀጠር ነበር ።ሰውየው አላስታወሱትም ።  በምን ፊልድ ነበር የምትሰራው ብለው ጠየቁት ፅዳት ሰራተኛ ነበርኩ ሰውየው ትዝ አላቸው ፡ ጥቂት ካወሩት በኋላ እና አሁን ምን ልርዳህ አሉት  የከተማ ፅዳት ሰራተኛ ፡  ከፈለጋችሁ ብዬ ነው።ቀጠሩት ። እና አሁን በለንደን ጎዳና ላይ ፡ አንድ ወፍራም ሰውዬ. ..  የፅዳት ስራ ሲሰራ ካያችሁት ፡ ያ ሰው ፡ በአንድ ወቅት ሚሊየነር የነበረውና ፡ ህይወት  የሰጠችውን እድል ሊጠቀምበት ባለመቻሉ ፡ ተመልሶ ፅዳት ሰራተኛ የሆነው ማይክል ካሮል እንደሆነ እወቁ ። ኢትዮ ካብ በአለማስተዋል የሚደረጉ ነገሮች መጨረሻ ላይ ዋጋ ሊያስከፍሉን  ይችላሉ ስለዚህ ሁሌም ቢሆን እናስተውል ፡፡ አንድ የሀገራችን አባባል አለ ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ ! የሚል  ሰለዚህም በህይወታችን የሚመጡ እድሎችን በአግብቡ እንጠቀምበት !!  ኢትዮ ካብም የሰጠንን መልካም ዕድል እንጠቀምበት !

ኢትዮ ካብ ስለሚሰጠው አገልግሎት ለማወቅ ድህረገጻችንን  www.ethiocab.com  ይጎብኙ

የ Driver application ለማውረድ http://driver.ethiocab.com እንዲሁም የ Customer application ለማውረድ  http://user.ethiocab.com

ኑ አብረን ሰርተን ትርፋችንን እንካፈል !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *