27 መስከረም 2023

ሞሮኮ እንደ አውሮፓውያኑ 2025 የሚካሄደውን የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ እንደምታዘጋጅ የአፍሪካ የእግርኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) አስታወቀ። ሞሮኮ ውድድሩን ለማሰናዳት የተመረጠችው ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ምቹ መሠረተ ልማት እና መገልገያ ባለማሟላት የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅነቷን የተነጠቀችውን ጊኒን በመተካት ነው። ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ታንዛኒያ ደግሞ በጋራ የ2027ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ተመርጠዋል። ከሁለት ዓመታት በኋላ የሚካሄደውን ውድድር ለማዘጋጀት በተካሄደው ምርጫ ላይ ዛምቢያ እንዲሁም ናይጀሪያ እና ቤኒን በጥምረት ተወዳድረው ነበር። ይሁን እንጂ አፍሪካ የዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት ያላትን ዕድል ይጨምራል በሚል ተስፋ ሞሮኮ እንድታዘጋጅ በመፍቀድ ከውድድሩ ወጥተዋል።

ሞሮኮ የ2030 የዓለም ዋንጫ በጣምራ ለማዘጋጀት ከተወዳደሩት ስፔን እና ፖርቹጋል ጋር እየተፎካከረች ነው። በዚህም የዓለም ትልቁን የእግር ኳስ ሁነት የምታዘጋጅ ሁለተኛዋ የአፍሪካ አገር ለመሆን ተስፋ አድርጋለች። ሞሮኮ የዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት ጥያቄ ስታቀርብ ይህ ለስድስተኛ ጊዜ ነው። የካፍ ውድድር አዘጋጆች ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞስቴፔ፣ “ለሁሉም ውድድሮች ያሉት አማራጮች አፍሪካን የሚያኮሩ ናቸው” ብለዋል። ፕሬዝደንቱ ጨምረውም ውሳኔው ሆስፒታሎች እና ሆቴሎችን ጨምሮ በአገራቱ በቀረቡት መሠረተ ልማቶች ደረጃ ላይ የተመሠረተ እንደሆነ ተናግረዋል። ሞስቴፔ እንዳሉት ውሳኔው በአፍሪካ አንድነት፣ እድገት እና ልማት ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን፣ የሞሮኮ ስኬትም አልጀሪያ በድምጽ መስጫው ዋዜማ ላይ ከውድድሩ ከወጣች በኋላ የመጣ ነው። “ለ2025ቱ ውድድር በርካታ ገንዘብ ሞሮኮ ላይ ይፈሳል። ሞሮኮ የዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት የተወዳደረችውም ለሞሮኮ ብቻ አይደለም፤ ለመላው አፍሪካም ጭምር ነው” ብለዋል ሞስቴፔ ። እንደ አውሮፓውያኑ 1976 ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ካዘጋጀት በኋላ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ታንዛኒያ ምሥራቅ እና ማዕከላዊ አፍሪካ የእግር ኳስ ማኅበርን ለመጀመሪያ ጊዜ ወክለዋል። ሦስቱ አገራት በጋራ ውድድሩን ለማሰናዳት በተካሄደው የምርጫ ፉክክር ላይ የተጣመሩት “መስፈርታችን እና ደረጃችን ከፍ ያለ ስለሆነ ነው” ብለዋል ሞትስፔ። “ውድድሩ በመሠረተ ልማት አንዳንዴ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ፣ አንዳንዴ ቢሊዮኖችን ይጠይቃል። በመሆኑም እግር ኳስ አገራትን በጋራ ማምጣቱ አኩርቶኛል። አፍኮን 2027 ትልቅ ስኬት ይሆናል” ብለዋል።ገልጿል። የሚወጡ አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት ድህረገፃችንን ይጎብኙ እንዲሁም ኢትዮ ካብ ስለሚሰጠው አገልግሎት ለማወቅ ድህረገፃችንን www.ethiocab.com ይጎብኙ !!

የ Driver application ለማውረድ http://driver.ethiocab.com  እንዲሁም የ Customer application ለማውረድ  http://user.ethiocab.com   

ኑ አብረን የሰራነውን አብረን እንካፈል የሚለን ኢትዮ ካብ ነው !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *