1 ጥቅምት 2023

ኢትዮጵያዊቷ ድርቤ ወልተጂ በላቲቪያ መዲና ሪጋ ዛሬ መስከረም 20/ 2016 . በተካሄደው አንድ ማይል የዓለም የሴቶች የጎዳና ላይ ሩጫ ክብረ ወሰን ሰበረች። ድርቤ 42100 የዓለምን ሪከርድ በመስበር አንደኛ ስትወጣ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ፍሬወይኒ ኃይሉ ሁለተኛ በመውጣት ብር አግኝታለች። ፍሬወይኒ ኃይሉ 42306 በመግባት የራሷን ምርጥ ሰዓት አስመዝግባለች። የአንድ ማይል ክብረ ወሰን ባለቤት የነበረችው እና ለአሸናፊነት ከፍተኛ ግምት የተሰጣት ኬንያዊቷ ፌይዝ ኪፕየጎን ደግሞ ውድድሩን በሦስተኛነት አጠናቃለች።

ባለፈው ዓመት መገባደጃ በቡዳፔስት በነበረው የዓለም ሻምፒዮና ውድድር ላይ 1500 ሜትር የብር ሜዳሊያ ባለቤት የሆነችው 21 ዓመቷ ድርቤ ይህንን ውድድር በድንቅ ብቃት እንዳጠናቀቀችም ተዘግቦላታል። ድርቤ ክብረ ወሰኑን ያሻሻለችው በቅርቡ በጀርመን በርሊን በተካሄደው 48ኛው የማራቶን ውድድር አትሌት ትዕግሥት አሠፋ የዓለም የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰንን ከሁለት ደቂቃ በላይ ማሻሿሏ ዓለምን እያነጋገረ ባለበት ወቅት ነው።

26 ዓመቷ አትሌት እንደ አውሮፓውያኑ 2019 በተካሄደው የችካጎ ማራቶን በኬንያዊቷ አትሌት ብሪጊድ ኮስጌ ተመዝግቦ የነበረውን 2:14.04 ከሁለት ደቂቃ በላይ አሻሽላለች። በዚህ የሪጋው ውድድር በአለም አቀፍ የሻምፒዮን ሺፕ ውድድሮች ላይ ብሮችን በማስመዝገብ የሚታወቀው ሐጎስ ገብረ ህይወት 5 ኪሎሜትር በአንደኛነት ሥፍራ ውድድሩን አጠናቋል። ሐጎስ በዚህ ውድድር ላይ 1259 ሰዓት አንደኛ የወጣ ሲሆን ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ዮሚፍ ቀጀልቻ 2ኛነት ውድድሩን አጠናቋል። ዮሚፍ ውድድሩን ያጠናቀቀበት ሰዓት 1302 ሲሆን ሁለቱን ኢትዮጵያውያንንም ተከትሎ ኬንያዊው አትሌት ኒኮላስ ኪፕኮይር ሦስተኛ ሆኗል። አትሌቶቻችን እያስመዘገቡ ባሉት ድል የተሰማንን ውስጣዊ ደስታ እየገለፅን !

ኢትዮ ካብ አብረውን በመስራት የትርፍ ተጋሪ ይሁኑ ይላል !! አብረውን የትርፍ ተካፋይ ለመሆን ወይም ስለምንሰጠው አገልግሎት ለማወቅ ድህረገፃችንን www.ethiocab.com ይጎብኙ !!

የ Driver application ለማውረድ http://driver.ethiocab.com  እንዲሁም የ Customer application ለማውረድ  http://user.ethiocab.com 

ከኢትዮ ካብ ጋር መስራት ባለቤትነት ነው!! 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *