ናይጄሪያ ውስጥ የሞተ ሰውን የራስ ቅል ከመቃብር ስፍራ ቆፍረው በማውጣት ወንጀል የተከሰሱ አምስት ሰዎች 12 ዓመት እስር ተፈረደባቸው። ሃብታም ለሚያደርጋቸው የአምልኮ ሥርዓት ማስፈጸሚያ አስፈላጊ ነው በሚል ወደ ጠንቋይ ለመውሰድ ሲሉ ነው የራስ ቅሉን ከተቀበረት ስፍራ በማውጣት ሊወስዱት አስበው ነበር ተብሏል። ግለሰቦቹ (ሁሉም ወንዶች ናቸው) የራስ ቅሉን በከረጢት ይዘው በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ጥፋተኛ መሆናቸውን አምነዋል። ዐቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው ከሆነ ግለሰቦቹ ከሦስት ዓመት በፊት በሰሜን ማዕከላዊ ናይጄሪያ ግዛት በሚገኝ የሙስሊም መቃብር ስፍራ የተቀበረ አስከሬንን ቆፍረዋል የራስ ቅሉን ወስደዋል።ጠንቋዩ ከወንጀል ድርጊት የተገኘን ሐብት እንደሚካፈሉ ለሁሉም ቃል በመግባት የራስ ቅል እንዲፈልጉ ነግሯቸዋልሲል ዐቃቤ ሕግን ጠቅሶ ዴይሊ ፓንች የተባለው የአገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧል።

መስከረም መጀመሪያ ላይ ነበር 18 እስከ 28 ዕድሜ ያላቸው እነዚህ ወጣቶች በጠንቋዩ ትዕዛዝ መሠረት የራስ ቅሉን በሌላ ሦስተኛ ወገን አማካይነት ሲያጓጉዙ በፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር የዋሉት። የናይጄሪያ ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ሚና የሚገኘው ፍርድ ቤት ግለሰቦቹን ለወንጀል በማሴር፣ የቀብር ቦታዎችን በማርከስ እና በሕገወጥ መንገድ የሰው ራስ ቅልን በመያዝ ጥፋተኛ ብሏቸዋል። ለዚህ ሁሉ ድርጊት ዋነኛው ተጠያቂ የሆነው ጠንቋይ ግን አስካሁን ያልተያዘ ሲሆን፣ ክስም እንዳልተመሠረተበት ታውቋል።

በጁጁወይምበቩዱወይምበጥንቆላ ማመን በናይጄሪያ የተስፋፋ ልማድ ነው። ይህንንም በርካቶች ከክርስትና ወይም ከእስልምና ጋር አጣምረው እንደሚያካሂዱት 2010 የወጣው የፒው የምርምር ማዕከል ሪፖርት ገልጿል። በተመሳሳይ መንገድ በተለይም የሰው አካል ክፍሎች ገንዘብ ማስገኝት ይችላሉ በሚል በናይጄሪያ በቅርቡ ለተስፋፉት አስከፊ ግድያዎች ምክንያት ሆኗል። ለዚህም በስፋት ዒላማ የሚደረጉት ደግሞ በቀላሉ ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑትን ሕፃናት፣ ያላገቡ ሴቶችን እና አካል ጉዳተኞችን መሆኑ ታውቋል።

የአካባቢው ባለሥልጣናት እንደተናገሩት ከሆነ የሰውነት ክፍሎች ሃብት ያስገኛሉ ተብሎ በሚታመንባቸው የአምልኮ ሥርዓቶች ለሽያጭ ይውላሉ። የዓለም ባንክ መረጃ እንደሚያመለክተው 10 ሰዎች አራቱ በድህነት በሚኖሩባት ናይጄሪያ፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣው የኢኮኖሚ መዳከም ገንዘብ ለማግኘት በሚል የሚከናወኑ የጥንቆላ ተግባራት ተስፋፍተዋል።

ኢትዮ ካብ ስለሚሰጠውአገልግሎት ለማወቅ ድህረገጻችንን  www.ethiocab.com ይጎብኙ

የ Driver application ለማውረድ http://driver.ethiocab.com እንዲሁም የ Customer application ለማውረድ  http://user.ethiocab.com 
ኑ አብረን ሰርተን ትርፋችንን እንካፈል  !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *