አፄ ኃይለ ሥላሴ ከባዝ ከንቲባ ዊሊያም ጋሎፕ ጋር 1954 (እአአ)

የጥቁሮች ታሪክ በሚከበርበት ብላክ ሂስትሪ መንዝመታሰቢያ በዓል የኢትዮጵያን የቀድሞ ንጉሥ አፄ ኃይለ ሥላሴን ከእንግሊዟ ከተማ ባዝ ጋር በማያያዝ የሚዘክር ሥነ ሥርዓት ተካሄደ። ይህ መታሰቢያ ንጉሥ ኃይለ ሥላሴ የባዝ ከተማን የነጻነት እውቅናን ካገኙበት 69 ዓመት ጋር በማያያዝ የኢትዮጵያውያን እና የራስ ተፈሪያን ማኅበረሰቦች የተለያዩ ዝግጅቶችን በማካሄድ ዘክረውታል።ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ጊዜ አፄ ኃይለ ሥላሴ በእንግሊዟ ባዝ ከተማ ውስጥ ፌርፊልድ ሐውስ በሚባል ስፍራ ከአውሮፓውያኑ 1936 አስከ 1941 ድረስ በስደት መኖራቸው ይታወቃል። ራስ ቤንጂ የተባለው የዝግጅቱ አስተባባሪንጉሥ ኃይለ ሥላሴ ከባዝ ጋር ያለቸውን ትስስርን በተመለከተ የለውን ግንዛቤ በሥነ ሥርዓቱ አማካይነት ከፍ እናደርጋለንብሏል። ጨምሮምሥነ ሥርዓቱን ባዝ ውስጥ ማክበራችን ለእኛ እጅግ ጉልህ የሆነ ትርጉም አለውብሏል። በሙሶሊኒ ይመራ የነበረው የጣሊያን ጦር ኢትዮጵያን መውረሩን ተከትሎ ንጉሠ ነገሥት አፄ ኃይለ ሥላሴ ከአገራቸው ተሰደው ነበር ወደ ባዝ የሄዱት።

አፄ ኃይለ ሥላሴ ለዓመታት ባዝ ውስጥ በስደት ቆዩ በኋላ ወደ አገራቸው ሲመለሱ የኖሩበት ፌርፊልድ ሐውስ የሚባለውን መኖሪያቸውን ለአረጋውያን መንከባከቢያ እንዲሆን ለከተማዋ በስጦታ አበርክተዋል። በየዓመቱ በአውሮፓውያኑ ጥቅምት ወር በሙሉ የሚታሰበው የጥቁሮች ታሪክ ወር ውስጥ የተለያዩ ዝግጅቶች ሲካሄዱ የቆዩ ሲሆን፣ አፄ ኃይለ ሥላሴ በስደት የኖሩበት ፌርፊልድ ሐውስ በባዝ እና በኢስት ሶመርሴት ምክር ቤቶች አማካይነት ሰፊ እድሳት ከተካሄደበት በኋላ ወሩን ሙሉ ለጎብኚዎች እሁድ እሁድ ክፍት ተደርጎ ቆይቷል።በተጨማሪም በየሳምንቱ እሁድ በተካሄዱት ጉብኝቶች ወቅት በአስጎብኚዎች አማካይነት የኢትዮጵያ ንጉሣውያን ቤተሰቦች ባዝ ውስጥ ስለነበራቸው ቆይታ እና አኗኗር ሲገለጽ ቆይቷል።ቅዳሜ በተካሄደው ክብረ በዓል ላይ ንግግሮች፣ ሥነ ግጥሞች የቀረበበት ሥነ ሥርዓት፣ በዲጄ የኢትዮጵያ እና የራስ ተፈሪያን ሙዚቃዎች የቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም ምግብ እና የተለያዩ ጨዋታዎች ተካሂደዋል።የዝግጅቱ አስተባባሪ ራስ ቤንጂ ንጉሥ ኃይለ ሥላሴን በዘከረው በዚህ ሥነ ሥርዓት ላይንጉሡ ባዝ ውስጥ ጥለውት ያለፉት ቅርስ አሁን ድረስ ሕያው መሆኑን እና ባሕላችንን ለማሳየት ተጠቅመንበታልብሏል።በተለይምባዝ ከተማ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትስስር ለማሳየት ፍላጎት ስላለን ነው ይህንን ዝግጅት ማቅረብ የፈለግነውሲል አክሏል።

ኢትዮ ካብ ስለሚሰጠው አገልግሎት ለማወቅ ድህረገጻችንን www.ethiocab.com ይጎብኙ

Driver application ለማውረድ http://driver.ethiocab.com  እንዲሁም Customer application ለማውረድ  http://user.ethiocab.com     

አብረን ሰርተን ትርፋችንን እንካፈል  !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *