9 ህዳር 2023

/ ማሕሙድ ሻሒን የጥርስ ሐኪም ነው። ሐሙስ ጥቅምት 8/2016 .. ድንገት ስልኩ ጠራ። የሞት ጥሪ ይሆናል ብሎ አልጠበቀም። በዚያ ላይ ገና ከጠዋቱ 1230 ነው። ሲፈራ ሲቸር፤ ስልኩን አነሳው።

ሐሎ፣ ከእስራኤል ደኅንነት ቢሮ ነበር የምደውለው። ያለህበትን ሕንጻ ልናጋየው ትዕዛዝ ተሰጥቶናል።/ ማሕሙድ ይህን ጥሪ ቀልድ ነው ማለትን መረጠ። ነገር ግን ከዚያች ዕለት በፊት ለተከታታይ 12 ቀናት እስራኤል በጋዛ ያሉ ሕንጻዎችን ወደ ትቢያነት ስትቀይር ነበር። ስለዚህ የስልክ ጥሪው ቀልድ ተብሎ ሊታለፍ አይችልም። የዶ/ ማሕሙድ ሰፈራቸው አል ዛሕራ ይባላል። በጣም ሰላማዊ ሰፈር ነው። መካከለኛ ገቢ ያላቸው ጋዛውያን የሚኖሩበት ሰፈር ነው። እሱ የሚኖረው በሦስተኛው ወለል፣ ሦስት መኝታ ቤት ባለው አንድ አፓርትመንት ነው። እስከዚያች የስልክ ጥሪ ዕለት ድረስ በጋዛ ያሉ ሁሉ ውድመት ሲደርስ በሰፈራቸው አንዲት ሕንጻ አልተነካችም ነበር።

ከእስራኤል ደኅንነት ነው የምንደውልልህ፣ ዶክተር። መፍጠን ይኖርብሃል።ይህ ጥሪ / ማሕሙድ በሕይወቱ ከተቀበላቸው የስልክ ጥሪዎች አስፈሪው ነበር።

ሦስቱን ሕንጻዎች አሁን ቦምብ ልንጥልባቸው ነው፤ ፍጠን

ከእስራኤል ደኅንነት የደወለው ሰው ጥርት ያለ አረብኛ ሲያወራ ድንቅፍቅፍ እንኳ አይልም። በእነርሱ ሰፈር ካሉ ሕንጻዎች ሦስቱን በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በቦምብ ሊያደባያቸው እንደሆነ ነገረው። እርግጥ ቦምብ ከሚጣልባቸው ሕንጻዎች መካከል የእሱ የለበትም። ነገር ግን ያልጠበቀው ኃላፊነት ወደቀበት፤ ዱብ ዕዳ።

ሰዎችን አስወጣ። ፍጥነት!” ተባለ። ደዋዩ የደኅንነት ሰው ራሱንአቡ ካሊድብሎ ነው ያስተዋወቀው። ድንገት የሦስት ሕንጻ ነዋሪዎች ነፍስ በዶ/ ማሕሙድ እጅ ላይ ወደቀ።

እባክህን ስልኩን አትዝጋው፣ አቡ ካሊድ/ ማሕሙድ ተማጸነ። 40 ዓመቱ የጥርስ ሐኪም / ማሕሙድ ለምን እስራኤሎች ለዚህ ተግባር እንደመረጡት አያውቅም። ብቻ ያን ቀን ነፍስ እንዳይጠፋ ነፍሱ እስኪጠፋ ተራወጠ። ከሕንጻ ሕንጻ፣ ከደረጃ ደረጃ እየዘለለእባካችሁ ፍጠኑ፤ ከሞት አምልጡ፤ እስራኤል ቦምብ ልትጥል ነውሲል ጮኽ። ጉሮሮው እስኪዘጋ፤ ላንቃው እስኪሰነጠቅ። ከዚያ ሦስቱ ሕንጻዎች ሁለቱ ወደ ትቢያነት ተቀየሩ። እዚያው በዐይኑ በብረቱ እያየ። ወር ባስቆጠረው የጋዛ ጥቃት እስራኤል ለጋዛውያን ከጥቃት በፊት የማስጠንቀቂያ ደውል አሰማለሁ ትላለች። አንዳንዴም ለግለሰቦች ስልክ ደውላ ሞት ጥላ እንዳጠላባቸው ትናገራለች። የዶ/ ማሕሙድ ታሪክም ይህን ያረጋግጣል።

አሁን በአል ዛሕራ ሰፈር / ማሕሙድ የሚታወቀውስልክ የሚደወልለት ሰውዬበሚል ሆኗል። የመጀመሪያው ቀን የስልክ ጥሪ የመጨረሻው አልሆነም። ስልክ በየቀኑ ይደወልለት ጀመር። ጠዋት ማታ፣ ነጋ ጠባ።

እስኪ አንዴ የማስጠንቀቂያ ተኩስ አሰሙኝ

ማሕሙድ በድጋሚ ሲደወልለት ማመን አልቻለም። አብረውት የነበሩት ሰዎችይህ ጥሪ የውሸት ሊሆን ይችላልይሉታል። ድጋሚ ሌላ ትዕዛዝ ሲሰጠው እና አብረውት ያሉትምየዉሸት ጥሪሊሆን እንደሚችል ሲነግሩት እሱም መጠራጠር ጀመረ። በሌላ ቀን ለደወለለት ሰው እስኪ እውነተኛ የእስራኤል ደኅንነት ከሆንክ የማስጠንቀቂያ ተኩስ ተኩስ ብሎ ጠየቀው። በዚያውም ማስጠንቀቂያው ደውሉን ሳይሰሙ የተኙ ካሉ ይነሳሉ በሚል ነበር በድፍረት ይህን የጠየቀው። ወዲያውኑ አንድ ከየት መጣ ያላለው ተኩስ (ምናልባትም ድሮን ይሆናል) ከአፓርትመንቶቹ አንዱን አነቃነቀው። / ማሕሙድ አሁን ነገሩ ሐቅ መሆኑን ተረዳ። እንደተለመደው ነፍስ ለማዳን መሮጥ ጀመረ።

እባክህን ትንሽ ደቂቃ ጨምርልኝ። እባክህን ስልኩን አትዝጋው/ ማሕሙድ ለእስራኤሉ ደኅንነት ተማጽኖውን አቀረበ።

እሺ ችግር የለውም፤ ግን ቶሎ ቶሎ እንዲወጡ አድርግ።

እባህክን ቃልህነት ጠብቅ፤ አትክዳን/ ማሕሙድ ተማጸነ። ደኅንነቱ ለዶ/ ማሕሙድ ተጨማሪ ደቂቃዎችን እንደሚሰጠው ቃል ገባለት።

ማንም እንዲሞት አንፈልግም፤ ቶሎ እንዲወጡ አድርግአለው ደኅንነቱ። / ማሕሙድ እንደተለመደው ከፎቅ ፎቅ፣ ከወለል ወለል እየሮጠ እየጮኽ ሕዝቡን ከሞት ለመታደግ የተቻለውን አደረገ። ሰዎችም በጩኽት ረዱት።

አንድም ሰው ቢሆን እኔ መልዕክቱን ሳላደርስ በዚህ ጥቃት ቢሞት ጸጸቱን አልችለውምይላል ማሕሙድ ለቢቢሲ። ከሕንጻዎቹ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወጥተው ደጅ ፈሰሱ። አንዳንዶቹ ፒጃማቸውን እንደለበሱ ናቸው። አንዳንዶቹ የጸሎት ልብስ እንደለበሱ ናቸው። ሰብሰብ ያሉበት አካባቢ የዋዲ ጋዛ ወንዝ ሰሜናዊ ክፍል ነው። ካፌዎች፣ ዩኒቨርስቲ፣ ፓርኮች ያሉበት ሰፈር ነው። በዚህ ፓርክ ነው አሁን የሰፈሩ ሰው ሰብሰብ ብሎ የቆመው። / ማሕሙድ ለምን ሰፈራቸው ዒላማ ሊሆን እንደቻለ አልገባውም።

ደኅንነቱን ላስቆመው ሞክሪያለሁ፤ ለምን የእኛን ሰፈር ዒላማ ታደርጋላችሁ፤ ለምን ብዬዋለሁ?” ይላል።

እሱም፣ምን መሰለህ፤ አንተ የማታያቸው፤ እኛ ግን የምናያቸው አንዳንድ ነገሮች አሉብሎ መለሰለት። ምን ማለቱ እንደሆነ ግን አላብራራም።

ይህ የበላይ ትዕዛዝ ነው፤ ከእኔም ካንተም በላይ የሆነ አካል ያዘዘው ነው። ስለዚህ በቦምብ እናጋየዋለን።/ ማሕሙድ ከሁሉም ሕንጻዎች ሰዎች መውጣታቸውን አረጋገጠ።

አሁን ማፈንዳት እንችላለን?” አለው ደኅንነቱ።

ይሄን ጊዜ / ማሕሙድ ደነገጠ።

ምናልባት እኔ ያላየሁት ሕንጻው ውስጥ የቀረ አንድ ሰው ቢኖርስ? አንዲት ሕጻን ብትኖርስ?”

እባክህን ትንሽ ታገሰን/ ማሕሙድ በድጋሚ ተማጸነ። በዚህን ጊዜ የእስራኤል የጦር ጄቶች አካባቢው ላይ ማንዣበብ ጀመሩ። ማሕሙድ ፈዞ ቀረ። ወዲያው ከሦስቱ ሕንጻዎች አንዱ በቅጽበት አፈር ትቢያ ሆነ። ይህ ሲሆን በዐይኑ በብረቱ ተመለከተ። ደኅንነቱ መናገር ጀመረ።

ይህን ሕንጻ ነው የፈለግነው። ትንሽ ራቅ በልአለው፤ ደኅንነቱ። ከዚያ ቀጥሎ ሁለቱ ሕንጻዎች አፈር ሆኑ። ልክ ፍንዳታው አልቆ ከአፍታ በኋላ / ማሕሙድ ስልኩ ጠራ።

ጨርሰናል፤ መመለስ ትችላላችሁብሎት ተዘጋ። / ማሕሙድ በጋዛ 15 ዓመታት ኖሯል። እንዲህ ዓይነት ጉድ አይቶም፣ ሰምቶም አያውቅም። የጥርስ ሐኪም ሆኖ ቀኑን በሥራ ተወጥሮ ልጆቹን ሲያሳድግ ነው የሚያውቀው። ሥራውን አብልጦ የሚወድ ባተሌ ነበር። አሁን ሥራ ማለት ምንም ማለት ሆነበት። የሕይወት ትልቁ ግቡ ነፍስን እስከ ነገ ማቆየት ነው።

ለደኅንነቱ ነግሬዋለሁ፤ አል ዛሕራ የንጹሐን መኖርያ ሰፈር ነው። ኮሽታ እንኳን አልነበረም። ማንም ወንጀለኛ በዚህ የለም። ለምን ማጋየት እንደፈለጉ አልገባኝም።

ከሦስቱ ሕንጻዎች ወደ አፈርነት መቀየር በኋላ ነዋሪዎች ሌላ መጠለያ ፍለጋ መንከራተት ጀመሩ። ቤታቸው በከፊል እንኳ የፈረሰባቸው ወደዚያው ወደ ፍርስራሹ ተመልሰው ገቡ። ሌሎች ደግሞ ሌላ መጠለያ ፍለጋ ተንከራረተቱ።

አንዳንዶች ወደ ፍርስራሹ ተመለስን፤ ደግመው መቼስ አያፈነዱትም አይደል?” የአየር ጥቃትን በመፍራት ነዋሪዎች ከቤታቸው ውጪ በምሽት ጎዳና ላይ

በማያውቀው ስልክ ቁጥርሚስኮል’’’

ያን ቀን ማታ / ማሕሙድ የምሽት ጸሎት (ኢሻ ሶላት) ሰግዶ ሲያበቃ ወደ ስልኩ ቢያማትርሚስኮልአገኘ።  ክፋቱ ደግሞ ቁጥሩ የማይታወቅ ቁጥር ‘private number’ ይላል። ልቡ በፍጥነት መምታት ጀመረ።በቃ ከደኅንነቱ ነው። ሊያፈነዱን ነው ማለት ነው።/ ማሕሙድ ያላወቀው እስራኤሎች የቱን ሕንጻ ቀጥሎ በቦምብ እንደሚያጋዩት ነው። እሱ በዚያ ስልክ መልሶ መደወል አይችልም። ሲደወልለት ብቻ ነው ማንሳት የሚችለው። ደግነቱ ወዲያው ስልኩ በድጋሚ ጠራ። በፍጥነት አነሳው፣ ሌላ ድምጽ ነው። ምናልባት የእስራኤል ደኅንነቶች / ማሕሙድ ብልህ ሰው መሆኑን ሳይረዱ አይቀሩም። ያን ቀን ማለዳ ብዙ ሕይወት አድኗል።

አዲሱ የእስራኤሉ ደኅንነትዳውድ አባላለሁሲል ራሱን አስተዋወቀው። / ማሕሙድ ደኅንነቱ ስለእሱ የሚያውቀው ዝርዝር ጉዳይ አስደነገጠው። ልጆቹን ጭምር በስም ያውቃቸዋል። አንድ በአንድ፣ ስለ ሕይወቱ አሳምሮ ያውቃል።

ተመልክተሃል ሐማስ ያደረገውን? የልጆችን አንገት…” ደኅንነቱ መናገር ጀመረ።

በእኛ እምነት ያን ማድረግ ክልክል (ሐራም) ነው። እናንተ እያደረጋችሁ ያላችሁት የጅምላ ቅጣት ነው/ ማሕሙድ የሚከራከረው በከንቱ እንደሆነ ገብቶታል። የእስራኤሉ ደኅንነት ምሽቱን በሰፈራቸው ተጨማሪ ሕንጻዎች ወደ አፈርነት እንደሚቀየሩ አረጋገጠለት። በፍጥነት ሰዎቹን ከሕንጻዎቹ እንዲለቁ እንዲያደርግ አዘዘው። መጀመሪያ የነገረው ዒላማ የሚደረጉት ሁለት ሕንጻዎች ብቻ መሆናቸው ነበር። ከዚያ ሦስት ናቸው ተባለ።

እሺ ጊዜ ስጠኝእባክህን/ ማሕሙድ ደኅንነቱን ተማጸነው። / ማሕሙድ ሮጠ፣ ሰዎችን ከሕንጻው እንዲለቁ አደረገ። አጠገቡ የነበረ ሕንጻም በጣም ተጠግቶ የተገነባ ስለነበር ከዚያም ሰው እንዲወጣ አደረገ። በዚህ ሰዓት አል ዛሕራ ሰፈር ጨለማ ውጦታል። ብዙዎቹ ነዋሪዎች የስልካቸውን ባትሪ ነው እየተጠቀሙ ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱት። አንድ አብዱላሒ ካቲብ የተባለ የአካባቢው ነዋሪ ለቢቢሲ ሲናገርውጡ እንባላለን፤ ወዴት እንደምንሄድ በጭራሽ አናውቅም። ምን መያዝ ምን መተው እንዳለብንም አናውቅምይላል። ማሕሙድ የቻለውን ያህል ደኅንነቱን እየተማጸነ ሰዓት አስጨመረ። ልክ በተባሉት ሕንጻዎች ነዋሪዎችን አስወጥተው እንደጨረሱ ሦስት ሕንጻዎቹ አፈር ሆኑ። በቃ አሁን አረፍን ሲሉ ድንገት ተደወለ።

ለውጥ ተደርጓል፤ በመደዳ ያሉት ሕንጻዎች በሙሉ አፈር ይሆናሉየሚል ትዕዛዝ መጣ። ይህ ማለት 20 ብሎኮች ውስጥ የሚኖሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በፍጥነት መውጣት አለባቸው። / ማሕሙድ ደዋዩን የእስራኤል ደኅንነትን ተማጸነ።እባክህን ሌሊቱን ጊዜ ስጠን። ሁሉንም አስወጥተን እናድራለን።

ሁለት ሰዓት ብቻ ሰጥቼሃለውስልኩ ተዘጋ። / ማሕሙድ ጊዜ አላባከነም። ከሕንጻ ሕንጻ እየሮጠ ሞት እያንዣበበ እንደሆነ ለፈፈ። ሰፈሩ በአንድ ጊዜ ተተረማመሰ። ስልክ ተደወለ። ዶ/ ማሕሙድ ተማጽኖ አቀረበ። ተጨማሪ ሰዓት ይሰጠኝ። ደኅንነቱ ድምጽ ላይ ምንም ስሜት አይነበብም።

ያሻህን ሰዓት ውሰድ፤ እንዲያውም አንተ ሳትፈቅድልን ሕንጻዎቹን አናጋያቸውምየእሰራኤሉ ደኅንነት ተናገረ።

እንዴት እንዲህ ትላለህ? ይህ በእኔ ፍቃድ የሚሆን አይደለም፤ በእኔ ፍቃድማ ቢሆን የቱም ሕንጻ እንዲጋይ አልሻምአለ / ማሕሙድ። ሰዓቱ ሊቃጠልበት ሆነ። በሰፈሩ አንድ አካል ጉዳተኛ አሮጊት ሴትዮ አሉ። ተረስተዋል። በመጨረሻው ብሎክ ነው የሚኖሩት። እሳቸውን ለማዳን ሩጫ ጀመረ። ደኅንነቱ ግንበቃ ሰዓት አልቋል፤ እናጋየዋለንአለ።

እያንዳንዱ ሕንጻ ፍርስራሽ መሆን ጀመረ። አንድ በአንድ።እጅግ አሳዛኝ ምሽት ነበር፤ ለመላው አል ዛሕራ ሰፈር ነዋሪዎችይላል / ማሕሙድ። ከቢቢሲ ጋር በዋትስአፕ ሁኔታውን ያጋራ ሌላ የአል ዛሕራ አንድ ነዋሪ በዚያ ሌሊት የነበረውን ጭንቅ እንዲህ ሲል ተናግሯል።

ወዴት መሄድ እንዳለብን አናውቅም፤ ግማሹ በሰፈሩ ያለ ትምህርት ቤት እንሂድ ይላል። ግማሹ ወደ አልኑሰይራት ስደተኞች ካምፕ እንሂድ ይላል። በዚያ መሀል ሌላ ፍንዳታ ይሰማል፤ ጭንቅ ነበር።/ ማሕሙድ ደኅነነቱን ጠየቀው።ወዴት እንሂድ?”

ወደ ምሥራቅ ውሰዳቸው።ወደ ምሥራቅ አደገኛ ነው፤ ሰዎች ከአሁን አሁን አለቀልን እያሉ ያሉበት ሰፈር ነው። ይህንኑ ስጋቱን ለደኅንነቱ በስልክ ነገረው።

በቃ ወደ ምዕራብ ውሰዳቸው።

ወደ ፓሊስታይን ጎዳና?”

አዎ።

ፓሊስታይን ዩኒቨርስቲ ብወስዳቸውስ?”

ደኅንነቱ ስልኩን ዘጋየጎረቤት ስልክ ጠራ

ዩኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ ኩርምት ብለው ተቀመጡ። በፍርሃት የሚርዱ ውሾች ያላዝናሉ። በእናቶች እና በሕጻናት መሀል ሆነው ተኮራምተው ቁጭ ብለው ይታያሉ። የሆነ ሰዓት ላይ የዶ/ ማሕሙድ ስልክ ጠራ።ባትሪህ ምን ያህል ይቀረዋል?” ከወዲያ በኩል ያለው ድምጽ ጠየቀ።“15% ብቻ/ ማሕሙድ መለሰ። ባትሪ ቆጥብ ብሎት ተዘጋ። ከዚያ ወዲያ በተከታታይ ይህንን ሕንጻ፣ ያንን ሕንጻ ልናጋየው ነው እያሉ ደወሉለት። / ማሕሙድ የስልኩ ባትሪ እየተሟጠጠ መጣ። ከዚያ ድንገት የጎረቤቱ ስልክ ጠራ።

ጎረቤቱ ስልኩን አነሳ።ከእስራኤል ደኅንነት ነው። / ማሕሙድን አቅርብተባለ።

/ ማሕሙድ እስከአሁን በሕይወት አለ። እንዲያውም የአካባቢው ሰዎች በደንብ አውቀውታል፤ ለይተውታል።ዶክተር እንዴት ነህ? ደወሉልህ እንዴ ዛሬ? ቀጥሎ የሚያፈነዱትን ሕንጻ ነግረውኻል? የቱ ነው?” ይሉታል።

የሞት መልዕክተኛውን፤ / ማሕሙድን።

ኢትዮ ካብ ስለሚሰጠው አገልግሎት ለማወቅ ድህረገጻችንን www.ethiocab.com ይጎብኙ

የ Driver application ለማውረድ http://driver.ethiocab.com  እንዲሁም የ Customer application ለማውረድ  http://user.ethiocab.com     

ኑ አብረን ሰርተን ትርፋችንን እንካፈል  !!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *