15 ህዳር 2023
“ኢትዮጵያ በ2026ቱ የአሜሪካ የዓለም ዋንጫ እንድታልፍ እፈልጋለሁ። የማይሳካ ቢመስልም ዕድል አለን።” ዮሐንስ ዘውዴ ከኮከብ ተጫዋቾች ጋር መቀራረብ ያለውን ጥቅም ከብዙዎች በላይ ያውቃል። በ1980ዎቹ አዲስ አበባ ተወልዶ ያደገው ዮሐንስ አስገራሚ ታሪክ አለው። በ10 ዓመቱ ከእናቱ ጋር ወደ ላስ ቬጋስ አቀና። ከዝቅተኛው የቬጋስ እርከን ላይ በመነሳት ለታዋቂ ስፖርተኞች የእረፍት ጊዜ አሳማሪ ለመሆን በቅቷል። በማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ ጭምር ነው። አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ስትራቴጂክ አማካሪ በመሆን ይሠራል። “በዚህ ሚና ላይ አሁን አራት ወር ሆኖኛል። ሥራዬ በፌደሬሽኑ እና በሌሎች ሊጎች፣ በፌዴሬሽኖች እና በብራንዶች መካከል መቀራረብን በመፍጠር ድልድይ መሆን ነው” ሲል ‘ጆኒ ቬጋስ‘ በመባል የሚታወቀው ዮሐንስ ለቢቢሲ ስፖርት ተናግሯል። “በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ብርሃን ለመፈንጠቅ፣ በአገራችን ያለውን እምቅ አቅምና ያለንን ሐብት እና ገጽታ ለለዓለም በማሳየት ‘መጥታችሁ ኢንቨስት ብታደርጉ አስደናቂ ነገር ታገኛላችሁ‘ ማለት ነው” ሲል ስለ ኃላፊነቱ ገልጿል።“ይህን ስፖርት የሚወዱ ብዙ ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶች አሉን። ትንሽ ማበርታት እና ትንሽ ዕድል ብቻ የሚፈልጉ ናቸው።” ከፓርኪንግ ሠራተኛነት እስከ እግር ኳስ ተጫዋች የእረፍት ፕሮግራም አቃጅነት ዮሐንስ አዲሱ ሙያው የተገናኙት ብዙዎች በማይገምቱት ምመልኩ ነው። በታዋቂው ቤላጂዮ ሆቴል እና ካሲኖ ውስጥ የመኪና ፓርኪንግ ሠራተኛ ይሠራ ነበር።“ምርጥ ጊዜ ነበር። እንደ ሊዮናርዶ ዲ ካፕሪዮ፣ ፍሎይድ ሜይዌዘር እና ማይክል ጆርዳን ያሉ ሰዎችን አይቻለሁ” ይላል የ36 ዓመቱ ዮሐንስ።
“በአንድ ወቅት አንድ ፈረንሳዊ የፊልም ተዋናይ መኪናውን አስነስቶ ሊወታ ሲል አገኘሁት። በጣም የምወደው ተጫዋች ፍራንክ ሪበሪ እንደሆነ ነገርኩት። እሱም ሪቤሪ ወንድሜ እንደማለት ነው አለኝ።“በሚቀጥለው ዓመት ስንገናኝ ግለሰቡ ሪቤሪ የፈረመበትን ማልያ እና ቁምጣ አመጣልኝ። ከዚያ በኋላ አንድ እኔ [የምንከባከበው] ሰው እንዳለ ነገረኝ። ጓደኛው በሆቴሉ ሲቀመጥ በምስጋና መልክ ክፍያውን ፈጸምኩኝ። “የነበረውን ነገር ጓደኛው ለተዋናዩ ነገረው። ተዋናዩ ‘ሁለት ወር ስጠኝ ላንተ ድንቅ ነገር አግኝቻለሁ’ አለኝ” ይላል።
“ከሁለት ወር በኋላ እቤት ከእናቴ ጋር ኦፕራን ስንመለከት ስልክ ተደወለልኝ። ‘ሃይ፣ ናስሪ ነኝ፣ ስለተዋወቅን ደስ ብሎኛል‘ አለኝ። እሱና እና ጓደኞቹ ወደ ቩጋስ እንደሚመቱ ነግሮ አንዳንድ ነገሮችን አመቻችቼ እጠብቀው እንደሆነ ጠየቀኝ።””ሳሚር ናስሪ አውቀው እንደሆነ እስከሚጠይቀኝ ድረስ አላወቅኩትም ነበር። ገረጣሁ፣ ተንቀጠቀጥኩ፣ አላበኝ” ሲል አጋጣሚውን ያስታውሳል።“ከዚያ በኋላ አንዱ ሌላውን መሳብ ጀመረ። ቲዎ ዋልኮት፣ ባካሪ ሳኛ፣ ኬራን ጊብስ እና መላው የአርሰናል ቡድን መጣ። የዮሐንስ ከበርካታ ስመ ጥር ሰዎች ጋር ሰፊ ትስስር ፈጥሯል። የኩባንያው የክሎውዳውት ስኬት እና በማህበራዊ ሚዲያዎች ያሉት ተጽእኖ በርካታ ዕድሎችን ፈጥሮለታል። በሰይፉ ፋንታሁን ሾው ላይ ለመታየትም በቅቷል። መሠረቱን ግን አልረሳም። ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ፤ ሲሄድ ጀምሮ ነበሩ ችግሮች አሁንም ባሉበት መኖራቸውን ተመለከተ። ያወጣው ዕቅድም ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ደጃፍ የሚያደርሰው ነበር። “እነዚህን አርአያ እና ለብዙ ኢትዮጵያዊን ህጻናት ኮከብ ከሆኑ ስፖርተኞች ጋር በመሥራት ስኬታማ ሆኛለሁ” ሲል ያስረዳል።“ልጅ እያለሁ በእነሱ ደረጃ ለመሆን እፈልግ እንደነበር አስታውሳለሁ። እኔ እዚያ ደረጃ ብደርስም ወደ ሀገሬ ስመለስ አሁንም ተመሳሳይ ችግሮች እንዳሉ አይቻለሁ።“
“በእግር ኳስ በኩል ለሰዎች ዕድሎችን ማምጣት ፈልጌ ነበር። ስለዚህ ግንኙነቴን በመጠቀም ሁሉም ሰው የማደግ ዕድል እንዲያገኝ ለመሥራት ከፌዴሬሽኑ ጋር ተነጋገርኩኝ። በእኔ ሃሳብ ተስማምተው የዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራን ሰጡኝ። የኢትዮጵያን እምቅ ሃብት መጠቀም በውጤት ረገድ የኢትዮጵያ የወንዶች ብሔራዊ ቡድን የተለያየ መልክ አለው። ዋሊያዎቹ በፊፋ የዓም ዋንጫ ተሳትፈው አያውቁም። በአፍሪካ ዋንጫ ለመጨረሻ ጊዜ ከምድብ ድልድል ያለፉት ኢትዮጵያ ባዘጋጀችው የ1968 የአፍሪካ ዋንጫ ነው። በውድድሩ አራተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል። አሁን ያለው ቡድን በሜዳው ከተጫወተ ከሁለት ዓመት በላይ ሆኖታል። ይህ የሆነው ባህር ዳር ስታደየምን ጨምሮ በአገሪቱ ያሉ 21 ስታዲሞች በቂ መሠረተ ልማቶች አላሟሉም በሚል በመታገዳቸው ነው። ቡድኑ በሜዳው ሊያደርግ የሚገባቸውን የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪኣ ጨዋታዎች በማላዊ፣ ሞዛምቢክ እና ሞሮኮ አከናውኗል። ዛሬ ለ2026 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከሴራሊዮን ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ በሞሮኮ ያከናውናል። እዚህ ጋር ነው ዮሐንስ ትልቅ ተጽዕኖ መፍጠር እንደሚችል የሚያምንበት ቦታ ነው። “በእርግጥ እኔ አሰልጣኝም፣ ቴክኒካል ዳይሬክተርም አይደለሁም” ይላል። “ኃላፊነቴ አገሮችን፣ ሊጎችን እና ብራንዶችን ከፌዴሬሽኑ ጋር ግንኙነት እንዲፈጥሩ ማድረግ ነው። በአሁኑ ወቅት በደጋፊዎቻችን ፊት አለመጫወታችን ይጎዳናል። ስለዚህ አሁን ብሔራዊ ቡድኑን መደገፍ ትልቅ ነገር ነው።“”ለተጫዋቾችም ተጨማሪ ሃብቶችን ያመጣልለ። የሚያሠለጥኑበትን ቦታ እንዲያገኙ በሮች ይከፈታል። ዝግጅታቸውን ያሻሽላል። የእኔ መኖር ያንን የስነ ልቦና ድጋፍ ለመስጠት ነው” የዮሐንስ ድጋፍ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ያደርጋታል ወይ የሚለው ወደፊት የሚታይ ቢሆንም የሚለፋው ግን ሞከረ ለመባል ብቻ አይደለም። እናም ‘ጆኒ ቬጋስ‘ ዕድሎቹን በሞከረ ቁጥር ሁሉም ነገር ይቻላል።
ኢትዮ ካብ ስለሚሰጠው አገልግሎት ለማወቅ ድህረገጻችንን www.ethiocab.com ይጎብኙ
የ Driver application ለማውረድ http://driver.ethiocab.com እንዲሁም የ Customer application ለማውረድ http://user.ethiocab.com
ኑ አብረን ሰርተን ትርፋችንን እንካፈል !!