ቤንጃሚን ኪፕላጋት፡ ኡጋንዳዊው አትሌት ኬንያ ውስጥ በስለት ተወግቶ ተገደለ

በሦስት የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ኡጋንዳን ወክሎ የተሳተፈው ቤንጃሚን ኪፕላጋት ኬንያ ውስጥ ሕይወቱ አልፎ መገኘቱን ዘገባዎች ጠቆሙ። የ34 ዓመቱ ኪፕላጋት በለንደን ኦሊምፒክ በሦስት ሺህ መሰናክል ተወዳድሮ እስከግማሽ ፍጻሜው ተጉዟል። ትውልደ ኬንያዊው አትሌት በኬንያዋ ኤልዶሬት ከተማ አቅራቢያ መኪና ውስጥ ደረቱ እና አንገቱ ላይ በስለት ተወግቶ ሕይወቱ አልፎ መገኘቱ ተዘግቧል። ኤልዶሬት በርካታ ኬንያዊያን አትሌቶች የወጡባትን እና ምርጥ የአትሌቶች ማሰልጠኛ […]

ከ24 ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያን በኦሊምፒክ የወከለው ፅጋቡ ግርማይ ከብስክሌት ሕይወት ራሱን አገለለ

የአውስትራሊያው ጄይኮ አሉላ የብስክሌት ቡድን ጋላቢ የነበረው ብስክሌተኛ ፅጋቡ ግርማይ ከብስክሌት ሕይወት ራሱን አገለለ። ከ24 ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያን በኦሊምፒክ መድረክ የወከለው ፅጋቡ በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች በግሉ እና ሃገሩን ወክሎ ተወዳድሯል። የአውስትራሊያው ጄይኮ አሉላ በኢንስታግራም ገፁ በለቀቀው መልዕክት ፅጋቡን ላበረከተው አስተዋፅዖ አመስግኖ በቀሪ ሕይወቱ መልካም እንዲገጥመው ተመኝቷል። በዓለም አቀፉ የሳይክሊንግ ማዕከል ተመልምሎ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ […]

ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን ያሳገደው አበረታች ቅመም እና በአገሪቱ ስፖርት ላይ የተደቀነው ስጋት

8 ታህሳስ 2023 በዓለም አቀፍ መድረክ ኢትዮጵያን በበጎ ከሚያስነሱ ጉዳዮች አንዱ ስፖርት ነው። በተለይም አትሌቲክስ። ከአትሌቲክስም ረዥም ርቀት ለአገሪቱ ስም ለአትሌቶቹ ደግሞ ክብር እና ጥሩ ገቢ የሚያገኙበት ነው። ይህ መልካም ስም ግን አልፎ አልፎ ጥቁር ነጥቦች እያጋጠሙት ነው። በቅርቡ ከአበረታች ቅመሞች ጋር በተያያዘ ስምነት አትሌቶች ቅጣት ተላለፎባቸዋል። ሁለቱ ደግሞ ከአበረታች ቅመሞች ጋር በተያያዘ ጊዜያዊ እገዳ […]

ክሪስቲያኖ ሮናልዶ የባይናንስ ማስታወቂያ በመሥራቱ የ1 ቢሊዮን ዶላር ክስ ተመሠረተበት

የእግር ኳስ ኮከቡ ክሪስቲያኖ ሮናልድ ግዙፉ የክሪፕቶከረንሲ መገበያያ የሆነው ባይናንስን በማስተዋወቁ የ1 ቢሊዮን ዶላር ክስ ተመሥርቶበታል። ክሱ እንደሚጠቁመው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ባይናንስን በማስተዋወቁ ኪሳራ የደረሰባቸው ሰዎች አሉ። በዚህ ምክንያት ለደረሰው ኪሳራ ተጫዋቹ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ካሳ እንዲከፍል ተጠይቋል። የሮናልዶን ኩባንያም ሆነ ባይናንስን አስተያየት እንዲሰጡ ያቀረበው ጥያቄ እስካሁን ምላሽ አላገኘም። በአውሮፓውያኑ ኅዳር 2022 ባይናንስ “ሲአር7” ሲል […]

ጆኒቬጋስ የእግር ኳስ ከዋክብት የእረፍት ጊዜያቸውን ለማሳመር የሚደውሉለት ኢትዮጵያዊ

15 ህዳር 2023 “ኢትዮጵያ በ2026ቱ የአሜሪካ የዓለም ዋንጫ እንድታልፍ እፈልጋለሁ። የማይሳካ ቢመስልም ዕድል አለን።” ዮሐንስ ዘውዴ ከኮከብ ተጫዋቾች ጋር መቀራረብ ያለውን ጥቅም ከብዙዎች በላይ ያውቃል። በ1980ዎቹ አዲስ አበባ ተወልዶ ያደገው ዮሐንስ አስገራሚ ታሪክ አለው። በ10 ዓመቱ ከእናቱ ጋር ወደ ላስ ቬጋስ አቀና። ከዝቅተኛው የቬጋስ እርከን ላይ በመነሳት ለታዋቂ ስፖርተኞች የእረፍት ጊዜ አሳማሪ ለመሆን በቅቷል። በማህበራዊ […]

የሊቨርፑሉ ተጫዋች ሉዊስ ዲያዝ አጋቾች አባቱን እንዲለቁት ተማፀነ

6 ህዳር 2023 ኮሎምቢያዊው የሊቨርፑል ተጫዋች ሉዊስ ዲያዝ አጋቾች አባቱን እንዲለቀቱና “ከስቃይ እንዲገላግሉት” ተማፅኗል። ግራ ዘመሙ ሽምቅ ተዋጊ ብሔራዊ ነፃነት ግንባር [ኢኤልኤን] ከቀናት በፊት የሉዊስን እናትና አባት ባራንካስ በተባለ ሥፍራ አፍነው መውሰዳቸው ይታወሳል። ነገር ግን እናቱ ቢገኙም አባቱ አሁንም አድራሻቸው አይታወቅም። እሑድ ከሉተን ሊቨርፑል ከሉተን ታውን በነበረው ጨዋታ ጎል ያስቆጠረው ሉዊስ ዲያዝ “ነፃነት ለአባቴ” የሚል […]

ቴን ሃግ ከማንችስተር ሽንፈት በኋላ ራሽፈርድ ልደት መደገሱ ተቀባይነት የለውም አሉ

4 ህዳር 2023 የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ ቡድናቸው በማንቸስተር ደርቢ ከተሸነፈ በኋላ የፊት መስመር ተጫዋቻቸው ልደት መደገሱ ተቀባይነት የለውም አሉ።  ማርከስ ራሽፈርድ ቡድኑ ዩናይትድ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት በማንቸስተር ሲቲ 3-0 ከተሸነፈ ከሰዓታት በኋላ የልደት በዓሉን ለማክበር በአደባባይ ታይቷል።  እሁድ ዕለት የነበረው የልደት ዝግጅት ቀድሞ የታቀደ ነበር። ዩናይትድ ‘አሳፋሪ’ በተባለ ሁኔታ በኦልትራፈርድ ሽንፈትን […]

ሊዮኔል ሜሲ ክብረ ወሰኑን ያራዘመበትን የባለንደኦር ሽልማት ለስምንተኛ ጊዜ አሸነፈ

31 ጥቅምት 2023 አርጀንቲናዊው የኢንተር ማያሚ አጥቂ ሊዮኔል ሜሲ ለስምንተኛ ጊዜ የወንዶች ባለን ደ ኦር አሸናፊ ሆነ።የ36 ዓመቱ ሜሲ ባለፈው ዓመት በተካሄደው የኳታር ዓለም ዋንጫ ሃገሩን ለክብር በማብቃቱ ነው ፓሪስ በተካሄደው ሥነ-ሥርዓት እውቅና ያገኘው። እንግሊዛዊው የሪያል ማድሪድ አማካይ ጁድ ቤሊንግሃም ከ21 ዓመት በታች ለሆኑ ተጫዋቾች የሚሰጠውን ኮፓ ዋንጫ አንስቷል። ሊዮኔል ሜሲ ክብረ ወሰኑን ያራዘመበትን ባለን […]

በውሰት ጫማ ከመሮጥ እስከ የማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት መሆን

  21 ጥቅምት 2023 አትሌት ኬልቪን ኪፕተም ከአምስት ዓመታት በፊት በመጀመሪያው የአገር ውስጥ ይፋዊ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሆነው በውሰት ጫማ ነበር። እአአ 2018 ላይ የመሮጫ ጫማ የመግዛት አቅም ስላልነበረው በውሰጥ ጫማ የአትሌቲክስ ውድድርን የጀመረው አትሌት ዘንድሮ የማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት መሆን ችሏል። ኪፕተም በዘንድሮ የማራቶን ውድድር 2 ሰዓት ከ35 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት በመግባት የዓለም […]

ኢትዮጵያውያኖቹ ትዕግሥት እና ጉዳፍ ለዓመቱ ምርጥ የዓለም ሴት አትሌት ሽልማት ታጩ

ኢትዮጵያውያኖቹ አትሌቶች ትዕግሥት አሰፋ እና ጉዳፍ ፀጋይን ጨምሮ ሦስት አፍሪካውያን አትሌቶች የዓለም አትሌቲክስ በየዓመቱ ለሚያዘጋጀው የዓለም ምርጥ ሴት አትሌት ሽልማት ታጩ። ከሁለቱ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተጨማሪ ኬንያዊቷ ፌይዝ ኪፕየጎን በዘንድሮው የዓመቱ የሴቶች የዓለም ምርጥ አትሌት ዕጩ ውስጥ ተካታለች። በአጠቃላይ ለሽልማቱ በዚህ ዓመት አስደናቂ ብቃትን ያሳዩ 11 አትሌቶች ዕጩ ሆነዋል። ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግሥት አሰፋ ባለፈው መስከረም ወር […]