ከአውስትራሊያ እስከ አሜሪካ፡ የምዕራባውያኑ የገና በዓል አከባበር በምስል

ምዕራባውያኑ የገና በዓልን እያከበሩ ይገኛሉ። በክርስትና እምነት ትልቅ ስፍራ ከሚሰጣቸው በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የገና በዓል በምዕራባውያኑ ዘንድ በድምቀት ይከበራል።                                            ቶኪዮ ጃፓን፡ የገና አባት ልብስ የለበሱ በጎዳናዎች ላይ ለልጆች ስጦታ ሲያበረክቱ።                       ሲድኒ አውስትራሊያ። በጀልባቸው ላይ ውሻ ይዘው እየተጓዙ ያሉት የገና አባት ከባሕሩ ዳርቻ ላይ ሆነው ለሚጠባበቋቸው ሰዎች ስጦት ይዘው ሲሄዱ።                  ማድሪድ […]

ጦርነት እንዲቆም በሚጠይቅ አጭር ፊልም ታዋቂ ሽልማትን ያገኘው ወጣት ኢትዮጵያዊ

አንዲት ወጣት መምህርት ወደ ማስተማሪያ ክፍል ስትገባ ፊልሙ ይጀምራል።“እንደምን አደራችሁ ተማሪዎች?” በማለት መምህርቷ ለተማሪዎቿ ሰላምታ ታቀርባለች። ዘለግ ያለው “ደህና እግዚአብሔር ይመስገን!” የሚለው የተለመደ የተማሪዎች ምላሽ ግን እዚህ ክፍል ውስጥ አይሰማም። ከዚያም መምህርቷ ቁጭ ብላ የተማሪዎቿን ስም መጥራት ትጀምራለች። ሄለን ተስፋዬ፣ ጋዲሳ ፍራኦል፣ ዊንታና ሐጎስ. . . እያለች ጥሪው ይቀጥላል፤ ምላሽ ግን የለም። ክፍሉ ውስጥ ያሉት […]

ታይም መጽሔት የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ ፈጣሪ ካላቸው አንዱ ቅዱስ አስፋው

30 ህዳር 2023 በታይም መጽሔት ከዓመቱ የአየር ንብረት ተጽዕኖ ፈጣሪ የዓለማችን 100 ሰዎች መካከል አንዱ በመሆን ተመርጧል፤ ቅዱስ አስፋው። የአካባቢ ቴክኖሎጂ ኩባንያ የሆነው ኩቢክ መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆነው ቅዱስ ‘የአየር ንብረት መሪዎች’ ተብለው ዝርዝሩ ውስጥ ከተካተቱት የዓለም የቢዝነስ መሪዎች አንዱ ነው። ቅዱስ ያቋቋመው ድርጅት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የፕላስቲክ ምርቶች ወደ ዝቅተኛ የካርበን ሕንጻዎች በመቀየር […]

በኢትዮጵያውያን እንቅስቃሴ የምትሞቀው የጂቡቲ መንደር – ፒካዶስ

24 ህዳር 2023 ፒካዱስ በረፈደ ቁጥር እየገረረች ሁሉንም የምትተናኮሰውን ፀሐይ ለመሸሽ የምትነቃው ማልዳ ነው። የምትችለውን ያህል ከውና ረፋዱ ላይ መልሳ ትተኛለች። ዳግም በንቁነት ወደ መታተር የምትመለሰው አመሻሹን ዘጠኝ ሰዓት ላይ ጉልበተኛዋ ፀሐይ ስትደካክምላት ነው። ከጂቡቲ ዋና ከተማ 12 ኪሎ ሜትር ያህል ተጉዘው ወደ ፒካዶስ ሲመጡ በስተግራ በኩል የኢትዮጵያን ሰሌዳ የለጠፉ የከባድ መኪና ተሽከርካሪዎች ተደርድረው ይታያሉ። […]

“ሐሎ! ከእስራኤል ደኅንነት ቢሮ ነበር የምደውለው። ቤትህን ልናጋየው ትዕዛዝ ተሰጥቶናል”

9 ህዳር 2023 ዶ/ር ማሕሙድ ሻሒን የጥርስ ሐኪም ነው። ሐሙስ ጥቅምት 8/2016 ዓ.ም. ድንገት ስልኩ ጠራ። የሞት ጥሪ ይሆናል ብሎ አልጠበቀም። በዚያ ላይ ገና ከጠዋቱ 12፡30 ነው። ሲፈራ ሲቸር፤ ስልኩን አነሳው። “ሐሎ፣ ከእስራኤል ደኅንነት ቢሮ ነበር የምደውለው። ያለህበትን ሕንጻ ልናጋየው ትዕዛዝ ተሰጥቶናል።”ዶ/ር ማሕሙድ ይህን ጥሪ ቀልድ ነው ማለትን መረጠ። ነገር ግን ከዚያች ዕለት በፊት ለተከታታይ […]

ዝናቸው ከኬንያ እስከ ኒውዮርክ የተሻገረው የ 84 ዓመቱ የ 1ኛ ክፍል ተማሪ

1 ህዳር 2023 እአአ 2004 ላይ ኪማኒ ማሩጌ የቀለም ትምህርት ፍለጋ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲመዘገቡ የዓለማችን በዕድሜ የገፉ አዛውንት ተማሪ ሆኑ። የ84 ዓመቱ አዛውንት ኬንያዊ ወታደር ነበሩ። የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት አስተዳደርን ተዋግተዋል። በልጅነት የትምህርት ዕድልን የተነፈጉት ኪማኒ፣ የኬንያ መንግሥት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትን ነጻ ሲያደርግ ማንበብ እና መጻፍ የምችልበት አጋጣሚ ይህ ነው በማለት ነበር በስተርጅና […]

ተመራማሪዎች የስድስት ሺህ ዓመታት ዕድሜ አለው የተባለ ጥንታዊ ጫማ አገኘን አሉ

29 መስከረም 2023 ከሳር ተሰርቶ ስድስት ሺህ ዓመታት ገደማ ዕድሜ አለው ተብሎ የተገመተ ጥንታዊ ጫማን በስፔን በአንድ ዋሻ ውስጥ ማግኘቱን ተመራማሪዎች አስታወቁ። በአውሮፓ ውስጥ ከተገኙ ቀደምት ጫማዎች መካከል በእድሜ ቀዳሚ ነው የተባለው ይህ ጫማ ስፔን ውስጥ በሚገኝ የሌሊት ወፎች ዋሻ ውስጥ ነው የተገኘው። በ19ኛው ክፍለ ዘመን በማዕድን አውጪዎች ተዘርፏ ከተባለው ዋሻ ውስጥ በርካታ የተለያዩ አይነት […]

የልዑል አለማየሁ ፀጉር እና ከመቅደላ የተዘረፈ ታቦት ለኢትዮጵያ ተመለሰ

22 መስከረም 2023 የልዑል አለማየሁ የፀጉር ዘለላና፣ ከመቅደላ ተዘርፎ የተወሰደ ታቦት እና የተለያዩ የኢትዮጵያ ቅርሶች ለኢትዮጵያ ተመላሽ ተደረጉ። በለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የልዑል አለማየሁ የፀጉር ዘለላ እና ከመቅደላ ጦርነት በኋላ በእንግሊዝ ጦር ተዘርፈው የተወሰዱ ቅርሶች መረከቡን ባወጠው መግለጫ አስታውቋል።  ኤምባሲው ከተረከባቸው ቁሶች መካከል ከመቅደላ የተዘረፈ የመድሃኒያለም ታቦት፣ የልዑል አለማየሁ የፀጉር ዘለላ፣ ከብር የተሰሩና በነሃስ የተለበጡ […]