ለአመታት በውሃ ችግር የሚፈተነው የወልቂጤ ከተማ ህዝብ ዛሬም ” የመንግስት ያለህ ” እያለ ነዉ…..

ችግሩን ለመፍታት ጥረት ላይ እየተደረገ ነዉ የሚለው የከተማው አስተዳደር በበኩሉ ” ሩጫ ላይ ነኝ ” ይላል። የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች የውሀ ጀሪካኖች በጫኑ ባጃጆችና ጋሪዎች ተሞልተዉ ይታያሉ። ሆቴሎች የሻወር አገልግሎትን ከረሱ የቆዩ ይመስላሉ። በአጠቃላይ ውሀ ቅንጦት መሆኑ ግለጽ ነዉ ይህን ጉዳይ ተመልክቶ የአካባቢዉን ማህበረሰብ ስለጉዳዩ የጠየቀዉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ሪፖርተር ችግሩ ለአመታት የቀጠለ መሆኑን ተረድቷል። እንደነዋሪዎቹ […]

ከአፍሪካ አየር መንገዶች በአውሮፕላን ብዛት ቀዳሚዎቹ የትኞቹ ናቸው?

የአየር ትራንስፖርት የሚሰጡ አየር መንገዶችን ማቋቋም እና በዘላቂነት በሥራ ላይ እንዲቆይ ማድረግ ከፍተኛ የገንዘብ አቅምን የሚጠይቅ የትራንስፖርት ዘርፍ ነው። ከአውሮፕላኖች ጀምሮ አየር መንገዶችን ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልጉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እንዲሁም ዋናውን ሥራ የሚሠሩትን ባለሙያዎች ለማግኘት እና ይዞ በትርፋማነት መቆየትም ከባድ ፈተና ነው። በርካታ የአፍሪካ አገር ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ በማፍሰስ የራሳቸው የአየር መንገድ እንዲኖራቸው በተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርጉም ኪሳራ […]

የ92 ዓመቱ ጉምቱ የሚድያ ባለሀብት ሮበርት ሙርዶክ ለስድስተኛ ጊዜ ቀለበት አሰሩ

አዛውንቱ የበርካታ መገናኛ ብዙኃን ባለቤት ሮበርት ሙርዶክ ከፍቅረኛቸው ጋር ትዳር ለማድረግ ቀለበት ማሰራቸው ተሰማ። የ92 ዓመቱ ሙርዶክ ከሩሲያዊቷ የ67 ዓመት የሞሌኪዩላር ባዮሎጂስት ኤሌና ዡኮቫ ጋር ለወራት በፍቅር ቆይተዋል። ሰርጉ በያዝነው ዓመት ካሊፎርኒያ በሚገኘው የሚሊየነሩ የተንጣለለ አዳራሽ እንደሚካሄድ ይጠበቃል። ይህ ከሆነ የዕድሜ እና የንዋይ ባለፀጋው ሙርዶክ ለአምስተኛ ጊዜ ጋብቻ ሊያደርጉ ነው ማለት ነው። ዜናውን ያወጣው ኒው […]

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን መከበር እንዴት ጀመረ፣ የመከበሩ አስፈላጊነት ምንድን ነው?

በየዓመቱ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በተመለከተ ከመገናኛ ብዙሃን ወይም በዙሪያዎ ካሉ ሰዎች ሰምተው ይሆናል። ነገር ግን ይህች ዕለት ለምን እንደምትከበር? መቼ እንደምትከበር? ዕለቷስ ክብረ በዓል ወይስ የአመፅ ቀን ? በተመሳሳይስ ዓለም አቀፍ የወንዶች ቀን አለ? በዚህ ዓመትስ ምን አይነት ዝግቶች ይኖራሉ? ለአስርት ዓመታት ያህል በዓለማችን የሚገኙ ሕዝቦች ማርች 8ን ለሴቶች ለየት ያለች ቀን እንደሆነች አድርገው […]

” ያንቺ እቃ ብቻዬን ጠላ እየሸጥኩ ያሳደኳቸውን 2 ወንድ ልጆቼን ይመልስልኛል ወይ ? “

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በታሪካዊቷ ዓድዋ ከተማ በነበረው የዓድዋ ድል በዓል  ላይ እምባ እየተናነቃቸው 😭 ንግግር አድርገው ነበር። እሳቸው በእንባ ንግግር ሲያደርጉ የበዓሉ ታዳሚ ህዝብ ከፍተኛ የሀዘን ስሜቱ ከፊቱ ይነበብ እንደነበር በስፍራው የነበረው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ገልጿል። ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ምን አሉ ? ” ዛሬ ወደ ትግራይ ስመለስ በህሊናዬ የሚመጡብኝ ብዙ ትዝታዎች አሉብኝ። ይቅርታ አድርጉልኝና አጋጣሚውን […]

ጋዜጠኛ ተመስገን “ትክክለኛ ፍትሕ ይሰጣሉ ብዬ ስለማላምን ይነሱልኝ” ያሏቸው ዳኛ “ #አልነሳም” አሉ….

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጥር 7 ቀን 2016 ዓ/ም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰሚ ችሎት ቀርበው በነበረበት ወቅት፣ “የግራ ዳኛ የሆኑት ክቡር አቶ አሕመድ መሐመድ ትክክለኛ ፍትህ ይሰጣሉ ብዬ ስለማላምን በዚህ ጉዳይ ከችሎት እንዲነሱልኝ ምክንቻቶቼን አቀርባለሁ” ብለው ያዘጋጁትን ምክንያታዊ ፅሑፍ በዝርዝር አቅርበው ነበር። ችሎቱም የጋዜጠኛውን አቤቱታ ካደመጠ በኋላ፣ የዳኛውን ከችሎት መነሳትና አለመነሳትን ጉዳይ ለመወሰን፣ ጋዜጠኛ ተመስገን በዋናው […]

 ” ፋኖን ታስጠልላላችሁ ” ፣  ” ለፋኖ አባላት ጥይት የማያስመታ መድኃኒት ትሰጣላችሁ ”  በማለት 11 የቅኔ ተማሪዎች ተገደሉ…..

በሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት በላይ ጋፊት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን 11 የቅኔ ተማሪዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በሜጫ ወረዳ ብራቃት ቀበሌ በሚገኘው በላይ ጋፊት  ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የአብነት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 11 የቅኔ ተማሪዎች  እንዲሁም 1 በግብርና የሚተዳደር የአካባቢው ነዋሪ ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተገድለው እንደሞቱ ተነግሯል። የሟች ቤተሰቦች […]

በሞተር ብስክሌት ላይ እስከ ሰኞ ገደብ ተጣለ….

በአዲስ አበባ ከነገ አርብ የካቲት 22/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ሰኞ የካቲት 25/2016 ዓ.ም እስከ ጠዋት 12:00 ሰአት ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ፍጹም  የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል። ቢሮው ክልከላው ለምን እንደተጣለ በግልፅ ያሳወቀው ነገር የለም። ክልከላው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን አያካትትም ተብሏል። የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶች ሆኑ አሽከርካሪዎች እስከ ተጠቀሰው […]

“ ከ4,000 በላይ ሴቶች ተደፍረዋል ” – የአማራ ክልል ሴቶች ማኀበር….

የኢትዮጵያ ሴቶች ማኀበር ሴቶች ላይ እየደረሱ ናቸው የተባሉ ፈርጀ ብዙ ችግሮችን በተመለከተ በየክልሉ በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማትን በመጋበዝ ትላንት ረቡዕ በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር። በዚህም ላይ ከተገኙት ባለድርሻ አካላት መካከል የአማራ ክልል ሴቶች ማኀበር አንዱ ነው። በአማራ ክልል በ “ፋኖ” ታጣቂዎችና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በየወቅቱ እያገረሸ የሚስተዋለውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ በሴቶችና ሕጻናት […]

የጋና ፓርላማ ከተመሳሳይ ፆታ ግንኙነቶች እና በዚህ ዙሪያ ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ጋር በተያያዘ በሚከሰሱ ሰዎች ላይ ጠንከር ባለ እስር የሚቀጣ ሕግ አጽድቋል….

አዲሱ ሕግ ምን ይላል ? ➡ በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ውስጥ መሆናቸውን የሚገልጹ እንዲሁም ሆነው የተገኙ ሰዎችን እስከ 3 ዓመት የሚደርስ እስር ፤ ➡ ቡድኖችን የሚያቋቁሙ እና በገንዘብ የሚደግፉ እስከ 5 ዓመት እስር እንዲቀጡ ያደርጋል። በአገሪቱ ሁለት ዋነኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተደገፈው እና ፓርላማው ያጸደቀው ይህ ሕግ ተግባራዊ የሚሆነው የጋናው ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ-አዶ በፊርማቸው ሲያጸድቁት ነው። ፕሬዝዳንቱ […]