”በኢትዮጵያ የዓይን ብሌን ቀዶጥገና የሚሰሩ ሀኪሞች 11 ብቻ ናቸው“

ቀደም ባለው ጥናት መሠረት እንኳ ከ300,000 በላይ ሰዎች በዓይን ጠባሳ ምክንያት የዓይን ብርሃናቸውን እንዳጡ በሚነገርላት ኢትዮጵያ የዓይን ብሌን ቀዶ ጥገና ሀኪሞች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ (የቀድሞው ብሔራዊ ደም ባንክ) አገልግሎት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጿል። ለተቋሙ ፈተና የሆነበት ጉዳይ ምን እንደሆነ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ […]

በሐዋሳ ከአንዲት ሴት ከ2 ሺህ በላይ የሐሞት ከረጢት ጠጠሮች በቀዶ ህክምና መውጣቱ ተገለጸ

በሐዋሳ በሚገኘው የፓነሲያ ሆስፒታል ከአንዲት ሴት ከ2 ሺህ በላይ የሐሞት ከረጢት ጠጠሮች መውጣቱን በቀዶ ሕክምናው ላይ የተሳተፉት የሕክምና ባለሙያ ለቢቢሲ ገለፁ። የ40 ዓመት ዕድሜ ካላት ከዚህች ግለሰብ 2ሺህ 94 የሐሞት ከረጢት ጠጠሮች በቀዶ ህክምና መውጣቱንም የፓነሲያ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ፀጋዬ ቸቦ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ዶ/ር ፀጋዬ በኢትዮጵያ እንዲህ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሐሞት ጠጠሮች […]

በኔዘርላንድስ ያለውን አሳሳቢ የአዛውንቶችን ብቸኝነት ለማቅለል ይረዳል የተባለው ሾርባ

ብቸኝነት በዓለም አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል። በኔዘርላንድስ አዛውንቶች ብቸኝነት እንዳይሰማቸው የሚያስችል እንቅስቃሴ በወጣቶች ተጀምሯል። በመዲናዋ አምስተርዳም ‘ኦማስ የሾርባ ሥራ’ በወጣቶች እና አዛውንቶች ጥምረት በብዙ ቦታዎች ተስፋፍቷል። ኢትዮ ካብ ስለሚሰጠው አገልግሎት ለማወቅ ድህረገጻችንን www.ethiocab.com ይጎብኙ የ Driver application ለማውረድ http://driver.ethiocab.com እንዲሁም የ Customer application ለማውረድ  http://user.ethiocab.com      ኑ አብረን ሰርተን ትርፋችንን እንካፈል  […]

“ሕክምና ለሁሉም ተደራሽ መሆን አለበት” ለቆዳ ካንሰር ሕክምና የሚሆን ሳሙና የሠራው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ታዳጊ

የዘንድሮው “የአሜሪካ ቁጥር 1 ታዳጊ ሳይንቲስት” ሽልማት አሸናፊ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሄማን በቀለ ነው። ሄማን ለቆዳ ካንሰር ሕክምና የሚሆን ሳሙና በመሥራቱ ነው የዚህ ጉምቱ ሽልማት አሸናፊ የሆነው። ላለፉት አራት ወራት የአሜሪካ ቁጥር አንድ ታዳጊ ሳይንቲስት ለመሆን ከሌሎች እኩዮቹ ጋር ሲፎካከር የነበረው ሄማን ለቆዳ ሕክምና የሚሆን ሳሙና በመፍጠር ከሌሎች ልቆ ተገኝቷል። ይህ ውድድር ከአምስተኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል […]

ሁለት የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች የደም ግፊትን እንደሚቀንሱ አንድ ጥናት አመለከተ

ግድግዳን በጀርባ ተደግፎ በዝግታ ቁጢጥ እንደ ማለት ‘ስኳት’ እና በክርን መሬት ላይ መላ ሰውነትን በመደገፍ የሚሰራው ‘ፕላንክ’ የተሰኙት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ዓይነቶች የደም ግፊትን ለመቀነስ ከሚረዱ መንገዶች መካከል ተመራጭ መሆናቸውን አንድ ጥናት አመለከተ። ለዘመናት ያህል በዋናነት መራመድ፣ መሮጥ እና ብስክሌት መጋለብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ላይ ትኩረት እንዲደረግ የተሰጡ ምክሮችም መሻሻል እንዲደረግባቸውም የዩናይትድ ኪንግደም ተመራማሪዎች እየተናገሩ […]

ኤችአይቪን የሚከላከለው መድኃኒት ውጤታማ መሆኑ በጥናት ተረጋገጠ

30 ህዳር 2023 ዌልስ ውስጥ በሙከራ ላይ የነበረውና በሰውነት ውስጥ የኤችኤይቪ ቫይረስ ሥርጭትን የሚገታው መድኃኒት ውጤታማ መሆኑ በጥናት ተረጋገጠ። የመድኃኒቱ ውጤታማነት የተረጋገጠው በመላው እንግሊዝ ከተውጣጡ እና በጥናቱ በተካተቱ ከ24 ሺህ በላይ የመድሃኒቱ ተጠቃሚዎች ላይ ምርመራ ከተካሄደ በኋላ ነው። በእንግሊዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ፒአርኢፒ የተሰኘውን ይህን መድኃኒት ከሥነ ተዋልዶ ጤና ክሊኒኮች እየወሰዱ ይገኛሉ። ከቼልሲ እና ዌስትሚኒስትር […]

የስኳር በሽታ ምንድነው ? እራሳችንን ከበሽታው እንዴት መጠበቅ እንችላለን ?

28 ህዳር 2023 የስኳር በሽታ ዕድሜ ልክ አበሮ የሚቆይ ሲሆን፣ በዓለም ዙሪያ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለሞት የሚዳርግ ከባድ ህመም ነው። ህመሙ የሚከሰተው ሰውነት በደምስር ውስጥ ያለን ስኳር (ግሉኮስ) በሙሉ በተገቢው መጠን ማመንጨት ሲያቅተው ነው። ይህም እንደ የልብ ድካምን፣ ስትሮክን፣ ዐይነ ስውርነትን፣ የኩላሊት ሥራ ማቆምን ሊያስከስት እና ከወገብ በታች ያለን የሰውነት ክፍል ላይ ከባድ […]

የጡት ካንሰርን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል ምሳሌ የሚሆኑት ኢትዮጵያዊት እናት

25 ጥቅምት 2023 ይህ የሆነው ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት ነው – በ1991 ዓ.ም.።የቤተሰብ ጋራዥ አስተዳዳሪ የነበሩት ወይዘሮ የወርቅውሃ ተከስተ ያኔ እድሜያቸው 42 አካባቢ ነበረ። አባታቸው በመታመማቸው ብዙ ጊዜያቸውን ሆስፒታል ውስጥ ያሳልፉ እንደነበር ያስታውሳሉ። እናም አንድ ቀን ከአባታቸው ጎን ተቀምጠው ሳለ የግራ ጡታቸው አካባቢ ለደቂቃ ያህል የቆየ ሕመም ተሰማቸው። ደንግጠው ጡታቸውን ነካኩ – የሆነ ጠጠር ያለ […]

አዲስ አበባ ውስጥ የሕክምና ባለሙያዎች ሥራ አጥነት አለ?

ከጥቂት ሳምንታት በፊት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገርያ የነበረው ጉዳይ የዶ/ር ናርዶስ አዱኛ ከቤት መጥፋት ነበር። በወቅቱ ከተመረቀች ዘጠኝ ወር የሆናት ዶ/ር ናርዶስ ‘የምትወዳቸውን ሁለት ልጆቿን ጥላ ጠፋች’ የሚለው ወሬ በርካቶች የተለያዩ መላምት እንዲሰጡ አድርጓቸዋል። ከዚያ በኋላ ዶ/ር ናርዶስ ጠፋች ከተባለችበት ስትመለስ፣ የሰጠችው ቃለ ምልልስ ላይ ለመሰወሯ ምክንያቱ ከሰባት ዓመታት ከባድ የሕክምና ትምህርት በኋላ ተመርቃ ሥራ […]

ሕጻናት ሳያቋርጡ እንዲተኙ ማሠልጠን ይጠቅማል?

ዌንዲ ሀል ካናዳዊ የእንቅልፍ አጥኚ ናቸው። ከስምንት ዓመት በፊት 235 ቤተሰቦችን ያማከለ ጥናት ሠርተዋል። ጥናቱ ልጆችን መተኛት ማስተማር ላይ ያተኮረ ነበር። ከስድስት እስከ ስምንት ወር የሆናቸው ሕጻናትን አሳትፏል።ቤተሰብ ልጆቹን ሳያባብል ልጆቹ በራሳቸው እንቅልፍ እንዲወስዳቸው ማድረግን ይዳስሳል። ወላጆች የተለያየ መንገድ በመጠቀም ልጆቻቸውን ያስተኛሉ። ልጆቹን ሳያባብሉ ለማስተኛት የሚጠቀሟቸው መንገዶችም አሉ። ልጆች ከተኙ በኋላ ሲነቁ ሳያባብሏቸው ልጆቹ ተመልሰው […]