በአዲስ አበባ ከነገ አርብ የካቲት 22/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ሰኞ የካቲት 25/2016 ዓ.ም እስከ ጠዋት 12:00 ሰአት ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ፍጹም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል።
ቢሮው ክልከላው ለምን እንደተጣለ በግልፅ ያሳወቀው ነገር የለም።
ክልከላው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን አያካትትም ተብሏል።
የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶች ሆኑ አሽከርካሪዎች እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ቢሮው አሳስቦ ይህን መልእክት በሚተላለፉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል ሲል አስጠንቅቋል።
ባለፈው ከአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ጋር በተያያዘ ለቀናት የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሎባቸው እንደነበር ይታወሳል።
በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon
ምንጭ ፡-@tikvahethiopia