በሦስት የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ኡጋንዳን ወክሎ የተሳተፈው ቤንጃሚን ኪፕላጋት ኬንያ ውስጥ ሕይወቱ አልፎ መገኘቱን ዘገባዎች ጠቆሙ።
የ34 ዓመቱ ኪፕላጋት በለንደን ኦሊምፒክ በሦስት ሺህ መሰናክል ተወዳድሮ እስከግማሽ ፍጻሜው ተጉዟል።
ትውልደ ኬንያዊው አትሌት በኬንያዋ ኤልዶሬት ከተማ አቅራቢያ መኪና ውስጥ ደረቱ እና አንገቱ ላይ በስለት ተወግቶ ሕይወቱ አልፎ መገኘቱ ተዘግቧል።
ኤልዶሬት በርካታ ኬንያዊያን አትሌቶች የወጡባትን እና ምርጥ የአትሌቶች ማሰልጠኛ ማዕከል ተብላም ትታወቃለች።
የኬንያ ፖሊስ በአሟሟቱ ዙሪያ ምርመራ መጀመሩን ገልጿል።
የዓለም አትሌቲክስ የኪፕላጋት ሞት “አስደንጋጭ እና አሳዛኝ” ሲል ገልጸታል።
አትሌቱ ሕይወቱ ያለፈለው እሑድ ምሽት መሆኑን ኤንቲቪ የተሰኘው የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።
ኡጋንዳዊው ወደ ቤቱ በሚወስደው መንገድ ላይ ሕይወቱ አልፎ መገኘቱን ጨምሮ ዘግቧል።
የሞኢቤን ፖሊስ ኮማንደር ስቴፈን ኦካል ከነዋሪው በደረሳቸው ጥቆማ እሑድ ጠዋት ስፍራውን መጎብኘታቸውን ጠቁመዋል።
ፖሊሶች አትሌቱ ደረቱ እና አንገቱ ላይ በስለት ጉዳት ደርሶበት አንዳገኙት ገልጸዋል።
መኪናው ጥቃት አድራሹ የተጠቀመበት እንደሆነ የተጠረጠረን ሞተር ሳይክል ገጭቶ እንደነበረም ተነግሯል።
“የተፈጠረውን ነገር ለማጣራት ክስተቱን እየመረመርን ነው። ማረጋገጥ የምንችለው ነገር ቢኖር ሞቶ የተገኘው ሰው ቤንጃሚን ኪፕላጋት የተባለ ዓለም አቀፍ አትሌት መሆኑን ነው” ሲሉ ኦካል ተናግረዋል።
በኬንያዋ ማራክዌት የተወለደው ኪፕላጋት ወደ ኡጋንዳ በማቅናት በተለያዩ ውድድሮች ላይ ተሳትፏል። ልምምዱንም በኤልዶሬት እና አካባቢው ሲሠራ ቆይቷል።
በተለያዩ መድረኮችም ኡጋንዳን ወክሏል። በሕንድ ደልሂ በ2010 በተከናወነው የኮመንዌልዝ ጨዋታዎችን አራተኛ ሆኖ አጠናቋል።
በ2011 የዓለም ሻምፒዮና 10ኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀ ሲሆን በ2012 የለንደን ኦሊምፒክም በሦስት ሺህ መሰናክል ግማሽ ፍጻሜ ላይ ደርሷል።
ኢትዮ ካብ ስለሚሰጠው አገልግሎት ለማወቅ ድህረገጻችንን www.ethiocab.com ይጎብኙ
የ Driver application ለማውረድ http://driver.ethiocab.com እንዲሁም የ Customer application ለማውረድ http://user.ethiocab.com
ኑ አብረን ሰርተን ትርፋችንን እንካፈል !!