![](https://ethiocab.com/wp-content/uploads/2023/09/photo_2023-09-10_00-17-04-1024x571.jpg)
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በግብፅ አቻው ተሸነፈ
On Sep 8, 2023
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ትላንት ምሽት በተካሄደው በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በግብፅ አቻው 1 ለ 0 ተሸንፏል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ2023 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ጨዋታ ከግብጽ አቻው ጋር አካሂዷል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች ጨዋታቸውን በካይሮ አየር ሃይል ስታዲየም ምሽት 1 ሰዓት ላይ አድርገዋል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ የግብጽ ብሄራዊ ቡድን ምድቡን በበላይነት አጠናቋል።
በአንጻሩ ዋልያዎቹ የማጣሪያ ውድድራቸውን በአራቱ ተሸንፈው አንድ አቻ በመውጣት እና አንድ ጨዋታ በማሸነፍ በአራት ነጥብ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።
ከኢትዮ ካብ ጋር መልካም አዲስ ዓመት ይሁንለላችው !!
ኢትዮ ካብ ስለሚሰጠው አገልግሎት ለማወቅ ድህረገጻችንን www.ethiocab.com ይጎብኙ
የ Customer application ለማውረድ http://user.ethiocab.com እንዲሁም
የ Driver application ለማውረድ http://driver.ethiocab.com ያገኙናል