አዲሱ ሕግ ምን ይላል ?

➡ በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ውስጥ መሆናቸውን የሚገልጹ እንዲሁም ሆነው የተገኙ ሰዎችን እስከ 3 ዓመት የሚደርስ እስር ፤

➡ ቡድኖችን የሚያቋቁሙ እና በገንዘብ የሚደግፉ እስከ 5 ዓመት እስር እንዲቀጡ ያደርጋል።

በአገሪቱ ሁለት ዋነኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተደገፈው እና ፓርላማው ያጸደቀው ይህ ሕግ ተግባራዊ የሚሆነው የጋናው ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ-አዶ በፊርማቸው ሲያጸድቁት ነው።

ፕሬዝዳንቱ ቀደም ሲል አብዛኛው የአገሪቱ ዜጎች የሚፈልጉት ከሆነ ሕጉን እንደሚያጸድቁት ተናግረው ነበር።

የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት በጋና ውስጥ ቀደም ብሎም ሕገወጥ ሆኖ በ3 ዓመት እስር የሚያስቀጣ ነው።

አዲሱ የጋና ሕግ በተለይ ህጻናት ላይ አተኩሮ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ለማስተዋወቅ በሚደረግ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የተሳተፈ ማንኛውም ሰው አስከ 10 ዓመት የሚደርስ እስር የሚቀጣ ነው።

ባለሥልጣናት “ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ” ለማስቻል ሕብረተሰቡ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ማኅበራት አባላትን እንዲጠቁሙ ሕጉ ያበረታታል።

ይህ ሕግ እንዲረቅ ምክንያት የሆነው ከ3 ዓመት በፊት በጋና ዋና ከተማ አክራ የመጀመሪያው የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የማኅበረሰብ ማዕከል መከፈቱን ተከትሎ እንደሆነ የፓርላማ አባላቱ ተናግረዋል።

ይህንንም ተከትሎ ብዙኃኑ ክርስቲያን በሆነባት ጋና የሃይማኖት እና ባህላዊ መሪዎች በፈጠሩት ግፊት ሕዝባዊ ተቃውሞ በመቀስቀሱ ፖሊስ ማዕከሉ እንዲዘጋ አድርጓል።

በወቅቱ የጋና የክርስትና እምነት ማኅበራት ባወጡት የጋራ መግለጫ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት “ ለአገሪቱ ባህል እና የቤተሰብ ዕሴት እንግዳ በመሆኑ የጋና ዜጎች ሊቀበሉት አይችሉም ” ሲሉ ተቀውመዋል።

የተለያዩ አገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የጋና ፓርላማ ያጸደቀውን ሕግ በመቃወም አስተያየት እየሰጡ ነው።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ፡-@tikvahethiopia

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *