በምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ጋና በሚገኘውቲቪ3′ የቴሌቪዥን ጣቢያ የሚተላለፈው የጋና ቆንጆ (Ghana’s Most Beautiful) የተሰኘው የሪያሊቲ ሾው መተላለፍ ከጀመረ 14 ዓመቱ ላይ ይገኛል።

በአገሪቱ ከፍተኛ ተመልካች ካላቸው የመዝናኛ ዝግጅቶችም አንዱ ነው። ለአራት ወራት በሚቆየው በዚህ ውድድር ላይም ተወዳዳሪዎቹ የተሰጣቸውን የቤት ሥራዎች አከናውነው ይመጣሉ። ውድድሩም ለሁለት ሰዓታት ይተላለፋል። በየዓመቱ በውድድሩ ላይ በመላው ጋና ከሚገኙ 16 ክልሎች ተወክለው የሚመጡ ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉበት ሲሆን፤ በጋና ውስጥ ስለሚገኙ የተለያዩ ትውፊቶች ለጋናዊያን ብሎም ለዓለም ሕዝብ ለማስተዋዋቅ ያለመ ውድድር መሆኑን አዘጋጁ ሚዲያ ግሩፕ የተሰኘው ተቋም ለቢቢሲ ገልጿል።

የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ክሪስ ኮኒ እንደሚሉት አፍሪካዊ አንድነትን በሚያንጸባርቅ መንፈስ የውድድሩ አንዱ ሳምንትየአፍሪካ ምሽትተብሎ ይሰየማል። ክሪስ አክለውም ተወዳዳሪዎች በዚህ የአፍሪካ ምሽት ላይ የሚወክሉትን አገር በዕጣ እንዲያወጡ የሚደረግ ሲሆን አዘጋጆቹ ተወዳዳሪዎቹ ከሚወክሉት አገር ዲፕሎማቶች ጋር እንዲገናኙ እና በዝግጅታቸውም እንዲረዷቸው እንደሚያግዟቸው ተናግረዋል።

በዚህ ዓመትም ከሰኔ ወር ጀምሮ 16 ተወዳዳሪዎችን ይዞ የጀመረው ጉዞ በመጪው ጥቅምት ወር ይጠናቀቃል።  ታዲያ በዚህ የአፍሪካ ምሽት ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ የናይጄሪያ እና ላይቤሪያን ጨምሮ የስምንት አገራት ትውፊት እና ታሪክ በተወዳዳሪዎቹ ቀርቧል።

ኢትዮጵያን ያስተዋወቀችው ዶክተር ሴቶር ማን ናት?

/ ሴቶር አብራ ኔግሮቤ በሞያዋ የህክምና ዶክተር ስትሆን የቮልታ ክልልን በመወከል ነው የጋና ቆንጆ ውድድር ላይ በመሳተፍ ላይ የምትገኘው። ሐኪሟ ሴቶር በተለይም አዕምሮ ጤናን በተመለከተ የተለያዩ የቅስቀሳ ሥራዎችን ታከናውናለች። ተሳታፊዎቹ ውድድሩ ከተጀመረ አንስቶ ከውጪው ዓለም ጋር አይገናኙም። ስልክም ሆነ ማንኛውንም አይነት የመገናኛ ዘዴ መጠቀም አይችሉም።

በዚህም ሳቢያ ቢቢሲ ሴቶርን አግኝቶ ለማናገር ያደረገው ጥረት አልተሳካለትም። ሴቶርን ጨምሮ ስምንቱም ተወዳዳሪዎች ወደሚወክለወቸው የአገራት ኤምባሲዎች በመጓዝ እና የአገራቱን ዜጎች በማነጋገር ለውድድራቸው ተዘጋጅተዋል።  ሴቶር ወደ ኢትዮጵያ ኤምባሲ በመሄድ ብሎም በጋና ዋና ከተማ አክራ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመነጋገር ለውድድሩ መሰናዳቷን ከአዘጋጆቹ ለመረዳት ተችሏል። የለበሰችውን ልብስ በማዘጋጀት ጭምርም ለውድድሩ እንዳገዟት ተናግረዋል። 28 ዓመቷ ሴቶር ባለፈው እሁድ ምሽት ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏ ብቻ ሳይሆን በምሽቱአንደበተ ርቱዕተብላም ተመርጣለች።

ውድድሩን አሸንፋለች?

ሴቶር ገና በውድድሩ አላሸነፈችም። የኢትዮጵያን ባሕል እና ታሪክ ባስረዳችበት ውድድርም ወደ መጨረሻው ዙር ካለፉት ሰባት ተወዳዳሪዎች መካከል ሆናለች። ከዚህ በኋላ ሁለት ውድድሮች ተደረጎ ነው የጋናዋ ቆንጆ የምትለየው።ሴቶር ለፍጻሜ ውድድር ለማለፍ የሚደረገው ውድድር ላይ ትሳተፋለች። ይህም በመጪው እሁድ ይሆናል። እርሱን ካለፈች መስከረም 23/2014 . ለሚደረገው ፍጻሜ ትበቃለች ማለት ነውሲሉ ክሪስ ለቢቢሲ ተናግረዋል።በዚህ ሳምንት ድጋፋቸውን ላሳዩን ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ምስጋናዬን ማቅረብ እፈልጋለሁ። እንደ ሕዝብ እርስ በእርስ ለመተዋወቅ እና ለመቀራረብ ጥረት እናድርግሲሉም ክሪስ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የዚህ ውድድር አሸናፊ አንድ ቅንጡ መኪና፣ ገንዘብ ብሎም ለአንድ ዓመት ያህል ብትን ጨርቅ ይቀርብላታል። 

ኢትዮ ካብ ስለሚሰጠው አገልግሎት ለማወቅ ድህረገጻችንን  www.ethiocab.com   ይጎብኙ

 የ Driver application ለማውረድ http://driver.ethiocab.com  እንዲሁም የ Customer application ለማውረድ  http://user.ethiocab.com    

    ኑ አብረን ሰርተን ትርፋችንን እንካፈል  !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *