ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጥር 7 ቀን 2016 ዓ/ም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰሚ ችሎት ቀርበው በነበረበት ወቅት፣ “የግራ ዳኛ የሆኑት ክቡር አቶ አሕመድ መሐመድ ትክክለኛ ፍትህ ይሰጣሉ ብዬ ስለማላምን በዚህ ጉዳይ ከችሎት እንዲነሱልኝ ምክንቻቶቼን አቀርባለሁ” ብለው ያዘጋጁትን ምክንያታዊ ፅሑፍ በዝርዝር አቅርበው ነበር።
ችሎቱም የጋዜጠኛውን አቤቱታ ካደመጠ በኋላ፣ የዳኛውን ከችሎት መነሳትና አለመነሳትን ጉዳይ ለመወሰን፣ ጋዜጠኛ ተመስገን በዋናው ክሳቸው ይሰጣሉ ተብሎ የሚጠበቀውን መለስ ለመቀበል ለጥር 28 ቀን 2016 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ አይዘነጋም።
ይሁን እንጂ ለጥር 28 ቀን 2016 ዓ/ም ተሰጥቶ የነበረው ቀጠሮ፣ “አቤቱታ የቀረበባቸው ዳኛ ስልጠና ላይ ስለሆኑ ውሳኔ አልሰጠንም” በሚል ለየካቲት 21 ቀን 2016 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶበት ተራዝሞ ቆይቷል።
በየካቲት 21 ቀን 2016 ዓ/ምቱ ችሎት ደግሞ፣ ጋዜጠኛው ከችሎቱ እንዲነሱ አቤቱታ ያቀረቡባቸው ዳኛ “አልነሳም” ብለዋል።
ጋዜጠኛው ያቀረቡት የዳኛውን “ከችሎት ይነሱልኝ” አቤቱታ ችሎቱ ወድቅ ያደረገው፣ “እንዲነሱ የተጠየቁት ዳኛ መልካም ስብዕና ያላቸው መሆኑን” በመጥቀስ ነው።
ጋዜጠኛ ተመስገን፣ የተሳሳተ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ዋቢ አድርገው በመጥቀስ “ዳኛው ይነሱልኝ” ብለው ባቀረቡት አቤቱታ ሳቢያ የ1,000 (አንድ ሺሕ ብር) ቅጣት ተፈርዶባቸው ክፍያውን ፈጽመዋል።
ጋዜጠኛው ተመስገን፣ ፍርድ ቤቱ ‹ዳኛው ስህተት ሰርተዋል ወይስ አልልሩም?› ወይም ‹ከሳሽ ያለአግባብ ጠቅመዋል ወይስ አልጠቀሙም?› በማለት የቀረበውን ቅሬታ መመርመሩን ወደ ጎን በመተውና የቀድሞ ስብእናቸውን መነሻ በማድረግ ቅሬታዬን ውድቅ ማደረጉ እጅጉን አስደንግጦኛል” ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም፣ “የፍርድ ቤቱ ትእዛዝ እኔን ስጋት ላይ የጣለ ነው” ያሉ ሲሆን፣ ጋዜጠኛው ላይ የቀረበውን የይግባኝ መልስ ለመስማትም ለመጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም ቀጠሮ ተስጥቷል።
በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon